ሸጊቱ ነገዎ፦
“2009 ዓም ሻሸመኔ ከተማ ነው የተያዝኩት። ሻሸመኔ ፓራዳይዝ ቫሊ ኮሌጅ ውስጥ ነበር የምሰራው። ሌላ ድርጅት ውስጥ አልሰራም። የተከሰስኩት ግን ሌላ ድርጅት ውስጥ የሚሰሩ ሰዎችን ሰብስበሽ ትሰሪያለሽ ተብዬ ነው። ……ማዕከላዊ በማላውቀው ጉዳይ ላይ ነው ተገድጄ የፈረምኩት። ጆሮዬ እስኪደማ ድረስ ተደብድቤ ተጎድቷል።ግራ እጄ ታሟል። በእግራቸው ነበር የሚረግጡኝ። ፀጉሬን እየጎተቱ ነበር የሚደበድቡኝ። ይደበድቡኝ የነበረው ያልሰራሁትን ነገር ሰርተሻል እያሉ ነው። እኔ ምንም የሰራሁት ነገር የለም። የሰጠሁት ቃል የለም። በግድ ነው የፈረምኩት። የደበደቡኝን መርማሪዎች ስማቸውን አላውቅም። ከቤ፣ ከቤ ነው የሚባባሉት። “
Comments»
No comments yet — be the first.