በ Ethiopia ከሰሞኑ ግጭትና አለመረጋጋት በስተጀርባ የህወሓት/TPLF እጅ አለበት! June 13, 2018
Posted by OromianEconomist in Uncategorized.Tags: Ethiopia, Ethiopia’s Liyyu Police – Devils on Armored Vehicles, Fascist TPLF Ethiopia, Genocidal mass killings against Oromo people in Eastern Oromia conducted by Liyu Police of TPLF Ethiopia, Liyu Police of Ethiopia, The study of Evil, TPLF
trackback
ከላይ በተጠቀሰው መሰረት፣ ላለፉት 27 ዓመታት በኢትዮጵያ ፖለቲካ ለረጅም ግዜ በስልጣን ላይ በመቆየታቸው ምክንያት በከፍተኛ የሞራል ዝቅጠት ውስጥ የወደቁት፣ በዚህም ሕግና ስርዓትን እንዲያስከብሩ የተሰጣቸውን ስልጣን ለሌብነትና የኮንትሮባንድ የሚያውሉት፣ እንዲሁም የዴሞክራሲያዊ መብትና ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ጥያቄ የሚያነሱ ዜጎችን በወታደራዊ ጉልበት የሚያዳፍኑት፣ በዚህም ፍርሃትና ሽብር በመፍጠር ሕገ መንግስታዊ ስርዓቱን ለማስከበርና ስልጣናቸውን ለማራዘም ጥረት የሚያደርጉት ህወሓትና ህወሓቶች አይደሉምን?
በአጠቃላይ ሰሞኑን በደቡብ ክልልና ሐረሪ፣ ከዚያ በፊት ደግሞ በቤኒሻንጉል-ጉሙዝ፥ ኦሮሚያ፥ አፋር፥…ወዘተ ግጭትና አለመረጋጋት የሚቀሰቀሰው በህወሓት ባለስልጣናትና ተላላኪዎቻቸው ነው። ምክንያቱም፣ አንደኛ፡- በዜጎች ላይ ሽብርና ፍርሃት በመፍጠር የፖለቲካ ትርፍ የሚያገኙት ህወሓቶችና የእነሱ ተላላኪዎች ብቻ ናቸው። ሁለተኛ፡- ላለፉት 27 አመት የተዘረጋው መንግስታዊ ስርዓት ሆነ የህወሓት ባለስልጣናት ያላቸው ተቀባይነት ከሕዝብ ፍቃድና ምርጫ ይልቅ በወታደራዊ ጉልበትና የበላይነት ላይ የተመሰረተ ነው። በመሆኑም በዜጎች ላይ ሽብርና ፍርሃት በመፍጠር ካልሆነ በስተቀር ተቀባይነት ሊኖረው አይችልም። ከዚህ አንፃር በተለያዩ የሀገሪቱ አከባቢዎች ለሚቀሰቀሱት ግጭቶችና አለመረጋጋቶች የህወሓቶች እጅ አለበት። በተለይ ከትላንት ጀምሮ ከወልቂጤና ሐዋሳ የሚመጡት መረጃዎች ይህንን የሚያረጋግጡ ናቸው።
ተቃ እና ተካ፦ “አያጅቦን ተባብረን እናባርረዋለን ወይም ነጣጥሎ ይበላናል!” ህወሓት መንግስታዊ ስርዓቱ በደቡብ አፍሪካ ከነበረው የአፓርታይድ ስርዓት የባሰ መሆኑንና የፖለቲካ ቡድኑም ፍፁም ቆሞ-ቀርና ፀረ-ለውጥ ነው. https://wordpress.com/read/feeds/83739448/posts/1893354097