jump to navigation

ሉዓላዊነት የቡድንም የግለሰብም ሥልጣን ነው፤ አታምታቱ!!! July 25, 2018

Posted by OromianEconomist in Uncategorized.
Tags: , , , , , , , ,
trackback

Odaa Oromoooromianeconomist


ሉዓላዊነት የቡድንም የግለሰብም ሥልጣን ነው፤ አታምታቱ!!!

Dr. Tsegaye Ararsa


ኢትዮጵያ ውስጥ “የቡድን (የብሔር-ብሔረሰቦች) እንጂ የግል መብት አይከበርም፤ የቡድኖች ሉዓላዊነት እንጂ የግለሰብ ሉዓላዊነት አይታወቅም” የሚል አምታች የቀማኛ ፖለቲከኞችና ፖለቲካ ተንታኞች ብሂል በተደጋጋሚ ይሰማል። ይሄ ትልቅ ስህተት ስህተት ብቻ ሳይሆን አውቆ ተሳስቶ ሰውን ማሳሳት ነው።

እውነቱ ግን ይህ ነው፦

1. ኢትዮጵያ ውስጥ በኢሕአዴግ የአፈና ሥርዓት ምክንያት አይተግበር እንጂ፣ በሕግ እውቅና ያልተሰጠው አንድም የግለሰቦች መብት የለም። የሕገ-መንግሥቱ ምዕራፍ 3 ከአንቀጽ 39 በቀር 30ው አንቀፆቹ የግለሰብን መብት ለማስከበር ተዘርዝረው የተቀመጡ ናቸው።

2. በኢትዮጵያ ውስጥ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች አባል ያልሆኑ ግለሰቦች ችግር ውስጥ ይወድቃሉ ይባላል። ሃቁ ግን፣ በኢትዮጵያ ውስጥ ከኢትዮጵያውያን ወላጆች የተወለደ፣ የአንድ ወይም የሌላ ብሔር አባል ያልሆነ ግለሰብ የለም።

የብዙ ብሔር አባል ከሆኑ ቤተሰቦች የተወለደ ሊኖር ይችላል እንጂ ብሔር-የለሽ ግለሰብ ሊኖር አይችልም፤ የለምም።

አንድ ግለሰብ፣ የብሔር አባል መሆን ስላልፈለገ የሚያጣው አንዳችም የግለሰብ መብት የለም፣ አይኖርምም። የብሔሮችን የቡድን መብት አለመጠቀም ይችላል። ለምሳሌ የቋንቋ፥ የባህል፥ የራስን ዕድል በራስ መወሰን መብትን ካልፈለገ አለመጠቀም መብቱ ነው። ይህንን አለመፈለጉንም፣ ድምፅ በሚሰጥበት ጊዜ በድምፁ የመግለፅ ሙሉ መብት አለው። ይኸም ግላዊ የራስን እድል በራስ የመወሰን መብትን (individual self-determination) ማስከበሪያ መንገድ ነው።

3. ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች የሉዓላዊነት ሥልጣን አላቸው (ቁ 8)። ይኼ ማለት፥

ሀ) በራሳቸው ገዳይ ላይ የመጨረሻ የመወሰን ሥልጣን የራሳቸው ነው ፤

ለ) ሌላ ማንም ኅይል በእነርሱ ጉዳይ ላይ አይወስንም (እነርሱ exclusive jurisdiction አላቸው) ማለት ነው።

ከዚህ ባሻገር እንደሉዓላዊነታቸው መጠን ከሌሎች የአገሪቱ ብሔሮች ጋር የአገረ-መንግሥቱ አቋቋሚና መስራች (co-founding) አእማድ (pillars) ናቸው ማለት ነው። የአገረ-መንግሥቱ ሉዓላዊ ሥልጣን ማህደር (local repositories) ናቸው ማለት ነው። ይህም በመሆኑ ሁሉም ቡድኖች በእኩል ደረጃ የሚገለፅ የአገረ-መንግሥቱ ባለቤትነት መብት (co-equal ownership of the state) አላቸው ማለት ነው።

ነገር ግን ይህ ስለሆነ በዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ውስጥ ሊኖር የሚገባው የግለሰቦች መንግሥታቸውን የማቆም፥ የመምራት፥ የመቆጣጠርና ሲበድላቸውም የማፍረስ ሥልጣን የላቸውም ማለት አይደለም።

ግለሰቦች በድምፃቸው (በምርጫ ጊዜም ይሁን በሬፈሬንደም ወቅት) ይህንን ግላዊ የሆነ የመጨረሻ ውሳኔ ሰጭነት ሥልጣን (sovereignty) ይጠቀማሉ። ይኼም፣ ግለሰቦች እንደ ዜጎች ያላቸውን ‘ግለሰባዊ ሉዓላዊነት’ እና ከዚህ የመነጨ የአገር ባለቤትነት መብት ያሳያል፤ ያረጋግጣል።

አንድ ሰው በድምፁ መንግሥትን መርጦ ከማቆም፣ ሲጠላውም ከመሻር የበለጠ ምን ዓይነት የሉዓላዊነት ሥልጣን እንዲኖረው ነው የሚፈለገው? ከዚህ ውጭ የሆነ ብሔር ዘለል ብሔርተኝነትስ (civic nationalism) ምን ዓይነት ነው? ይዘቱስ ምንድነው?

የእነዚህ ፖለቲከኞችና የፖለቲካ ተንታኞች ‘civic nationalism’፣ ይዘቱ civic nationalism ሳይሆን የቡድን መብቶችን ለመካድ፣ ቢቻል ደግሞ ለመሻር ከመፈለግ የመነጨ፣ ጉዳዩን የማድበስበስና የማምታታት ንግግር ነው። በተለይ ስለፊንፊኔ ባለቤትነት ጉዳይ በሰፋሪ ልሂቃን ሲቀነቀን፣ ዓላማው የኦሮሞን የባለቤትነት ጥያቄ ለመካድ የሚደረግ የብልጣብልጦች ዘመናዊ ተረት መሆኑን ልብ ይሏል።

Comments»

No comments yet — be the first.

Leave a Reply

Please log in using one of these methods to post your comment:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

%d bloggers like this: