jump to navigation

Ethiopia: የህወሓቶች ገበና ሲጋለጥ፤ እንደ ወራሪ ጦር የዘረፉት መሬት፣ እንደ ጠላት የትም የበተኑት ገንዘብ! (አፈትልኮ የወጣ ሰነድ) December 4, 2018

Posted by OromianEconomist in Uncategorized.
Tags: , , , , , , , , , , ,
trackback

የህወሓት ዘረፋና የመሬት ወረራ የተጀመረው ገና በትግል ላይ ሳለ ነው። በትግል ወቅት በቁጥጥሩ (ምርኮ) ስር የወደቁ ማናቸውንም ዓይነት ንብረትን የመውረስና ወደ ትግራይ ክልል ሰብስቦ የመውሰድ አባዜ ነበረው። ነገር ግን በዚህ መልኩ ተዘርፎ የሚወሰድ ሃብትና ንብረት ለህወሓቶች በቂ ወይም አጥጋቢ ሆኖ ባለመገኘቱ ከቁሳዊ ሃብት ይልቅ የከተማና ለም የሆኑ የእርሻ መሬቶችን መዝረፍ ጀመረ። የመሬትን ዘላቂ ጥቅምና አዋጭነት የተረዱት ህወሓቶች በ1984 መጀመያ አካባቢ በሰሜን ጎንደርና ወሎ ያሉ ለም የእርሻ መሬቶች ያሉበት ሁመራና ራያ በትግራይ ክልል ስር እንዲጠቃለል አደረጉ።

በመቀጠል በደርግ መንግስት ስር ይተዳደሩ የነበሩ የሜካናይዝድ የእርሻ መሬቶችን፣ ማሽኖችን፣ የባንክ ገንዘቦችን፣ በአጠቃላይ በወቅቱ በመንግስት ቁጥጥር የነበሩ ንብረቶችን “በኢንዳውመነት” ስም እንዲመዘገብ አደረጉ። በመቀጠል በተለያዩ የሀገሪቱ ክልሎች የሚገኙ የእርሻ መሬቶችን በኢንቨስትመንት ስም ተቆጣጠሩ። በዚህ መሰረት በጋምቤላንና አፋር ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ፣ አብዛኛው የቤንሻንጉል-ጉሙዝ የእርሻ እና የከተማ መሬቶች፣ በደቡብ ኦሞ የመንግስት እርሻ ቦታዎች፣ የሆቴል እና የመኖሪያ ቦታዎች፣ በመተማና ጎጃም እርሻ ልማቶች፣ እንዲሁም በአዲስ አበባ እና ዙሪያዋ የሚገኙ ጥሩ የኢንቨስትምት እና የማዕድን ቦታዎችን ያለ ተቀናቃኝ በበላይነት ተቆጣጥረዋል።

በዚህ ተግባር የተሰማሩት ሰዎች የአንድ መንደር ተወላጅ የሆኑ የህወሓት አባላት ናቸው። እነዚህ መንደርተኞች በድብቅ መሬት እንዲወስዱ የተደረገው በወቅቱ የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስተር በነበሩት በአቶ መለስ ዜናዊ ትዕዛዝ ነው። አሁንም እየዘረፉና ሃብቱን እያሸሹ ያሉት እነዚህ ሰዎች ናቸው። ይህን ለማረጋገጥ በኢትዮጵያ ልማት ባንክ አማካኝነት ከዋናው መስሪያ ቤት እስከ ቅርንጫፍ የተሠጡ ብድሮችን፣ እንዲሁም በብድር ማስታመሚያና ማገገሚያ ክፍሎች ያሉት ፕሮጀክቶች የእነማን እንደሆኑ በመመርመር እውነታውን መገንዘብ ይቻላል፡፡

Click here to read the full article

Comments»

1. OromianEconomist - December 8, 2018

በእርግጥ ብዙዎቻችን ባለፉት አመታት ከፍተኛ ዘረፋና ሌብነት ሲፈፅሙ የነበሩት ሰዎች ከፍተኛ የህወሓት አመራሮች እና ጄኔራሎች ይመስሉናል። በዚህ የወንጀል ተግባር የተሰማሩት አመራሩ ብቻ ሳይሆን ብዛት ያላቸው የህወሓት አባልና ደጋፊ የሆኑ የትግራይ ተወላጆች ናቸው። በዛሬው ዕለት በተካሄደው የተቃውሞ ሰልፍ ላይ ኢትዮጵያ ውስጥ ተወልደው ሱዳን የሚቀላውጡት፣ በተግባር የማያውቁትን ሕገ-መንግስት ይከበር የሚሉት፣ እንዲሁም ከዘረፏት ሀገር ክብርና ውዳሴ የሚሹት እነዚህ ሌቦች ናቸው። https://ethiothinkthank.com/2018/12/08/tplfs-corruption-scandal-in-afar-region/

2. OromianEconomist - December 9, 2018

የህወሓት አባላትና አመራሮች የሚያሳዩት ባህሪና የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ ለብዙዎች ግልጽ አይደለም። ብዙሃኑ የህብረተሰብ ክፍል የተቀበለውን ለውጥ እነሱ ይቃወሙታል። በሀገራችን የተጀመረው ለውጥ በብዙሃኑ ዘንድ ድጋፍና ተቀባይነት ሲያገኝ ህወሓቶች ግን ሲያጣጥሉትና ሲቃወሙት ይስተዋላል። ብዘሃኑ የህብረተሰብ ክፍል ስለ ስላም ሲናገር እነሱ ስለ ጦርነት ይዘምራሉ። የህወሓት አባላትና ደጋፊዎች ለውጡን የሚቃወሙበት መሰረታዊ ምክንያት ምንድነው? በእርግጥ ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚንቀሳቀሱ ሌሎች የፖለቲካ ቡድኖች ለየት (የተለየ) የሚያደርጋቸው ነገር አለ?

የችግሩ መሰረታዊ መንስዔ ያለው የህወሓት ዓላማና ግብ የአንድ ወገን የበላይነትን ማረጋገጥ መሆኑ ላይ ነው። ህወሓት እንደ ግለሰብ የድርጅቱን አመራሮች፣ እንደ ቡድን የድርጅቱን አባላት፣ እንደ ማህብረሰብ ደግሞ የትግራይን ህዝብ የበላይነት እና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ዓላማ አድርጎ የተመሰረተ ነው። ይህ ከደደቢት እስከ ቤተ-መንግስት፣ ከአዲስ አበባ እስከ መቀሌ ድረስ ያለና የነበረ የድርጅቱ መሰረታዊ አቋምና መርህ ነው። ስለዚህ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ የህወሓት ዓላማና ግብ የራሱን የበላይነትና ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ነው።

በህወሓት መሪነት የተዘረጋው መንግስታዊ መዋቅር፣ ተቋማትና የአሰራር ሂደቶች በሙሉ የራሱን የበላይነትና ተጠቃሚነት በማረጋገጥ ላይ መሰረት ያደረጉ ናቸው። ነገር ግን የትግራይ ህዝብ፣ የህወሓት አባላትና አመራሮች ከአጠቃላዩ የኢትዮጵያ ህዝብ፣ በሀገሪቱ ከሚንቀሳቀሱ ሌሎች የፖለቲካ ድርጅቶች አንፃር ሲታይ አናሳ (Minority) ነው። በመሆኑም እንደ ፖለቲካ ድርጅት ሆነ ማህብረሰብ የህወሓት ዓላማና ግብ ብዙሃኑን (Majority) የሀገሪቱን ህዝብና የፖለቲካ ቡድኖች ያገለለ ነው።

በዚህ መሰረት ህወሓት የራሱን የበላይነትና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚያደርገው ነገር በሙሉ የብዙሃኑን እኩልነትና ፍትሃዊ ተጠቃሚነት የሚፃረር ይሆናል። ህወሓት እንደ ድርጅት የተመሰረተበትን ዓላማና ግብ ለማሳካት ጥረት ባደረገ ቁጥር የብዙሃኑን መብትና ተጠቃሚነት የሚጋፋ ተግባር ይፈፅማል። https://ethiothinkthank.com/2018/12/09/ethiopia-and-tigray-singing-for-peace-and-war/


Leave a Reply

Please log in using one of these methods to post your comment:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

%d bloggers like this: