jump to navigation

የመጨረሻው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስተር? July 24, 2020

Posted by OromianEconomist in Uncategorized.
trackback

የመጨረሻው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስተር?

By Tullu Liban

የአማራ ኤሊቶች የብሔር ፖለቲካን በብሔር ተደራጅተው የሚቃወሙ ጉዶች ናቸው። አንድ ነገር በግልፅ መነጋገር ያስፈልጋል። የኢትዮጵያ ፖለቲካ ድሮም የዘር ፖለቲካ ነው። እንደዛሬው በግልፅ ሳይ ነገር “ኢትዮጵያዊ” ሽፋን ተሰጥቶት ሳይገለጥ ለብዙ ጊዜ ቆይቷል። አሁን ግን ጎራ ለይቷል። ጎራው ርዕዮተ ዓለማዊ አይደለም፤ ብሔር ነው። በአማሮችና አማራ ባልሆኑት መካከል ሆኗል ግብግቡ። የአጼ ኃይለሥላሴን ወይም የደርግን አገዛዝ መሰል የአስተዳደር ዘይቤ ለመመለስ የሚፈልጉ ኃይሎችና ባንድ ወገን ተሰልፈዋል። ኢትዮጵያዊ ካባ አጥልቀው ቢንቀሳቀሱም እኛ በትክክለኛ ስማቸው አማራ ብለን እንጠራቸዋለን። እነዚህ ኃይሎች አሁን በሥራ ላይ ያለው ህገመንግሥት ዋና ጠላታቸው ነው። በሌላ አንፃር ደግሞ አሁን ያለው ህገመንግስት በትክክል እንዲተገበር በሚፈልጉ ኃይሎች ተሰልፈዋል። ፊልሚያው በሁለቱ መካከል ነው።የአማራ ፖለቲከኞችና ተከታዮቻቸው የብሔር ፖለቲካን የዘር ፖለቲካ ይሉታል። አሁን ያለውን የክልሎች ራስን የማስተደደር ጥያቄ የሁሉ ችግር መነሻ አድርገው ይመለከቱታል። የሚገርመው ግን የክልል የራስ አስተዳደርን የሚቃወሙት በዘር ተደራጅተው ነው። ሰሞኑን ለአብይ የድጋፍ ሰልፍ የሚወጣውን ማህበረሰብ ማየት በቂ ነው። አማሮች ናቸው። ጥቂት የማንነት ቀውስ የሚያጠቃቸው ከኦሮሞና አማራ ተወልደው በአማራ ስነልቦና የታነፁ ሰዎችም አሉበት። የድጋፍ ሰልፍ ማውጣታቸው ባልከፋ። እየከፋ ያለው ነገር ኦሮሞን ግደልልን፣ እሰርልን፣ አፍንልን መባሉ ነው። ወያኔን ደምስስልን ማለታቸው ላይ ነው። የአማራ ኤሊቶች አቋም በዳንኤል ክብረትና የማንነት ቀውስ ባላቸው በነ ካሳዬ ጨመዳ፣ ዮናታን ተስፋዬና፣ አስቴር በዳኔ፣ ታምራት ነገራ በኩል እየተነገረን ነው። ክልሎችን ማፍረስ የኦሮሞን መሪዎች ማስወገድ የድጋፋቸው ማጠንጠኛ ነው። ጥያቄው ግን ክልሎቹን አፍርሰው አማሮቹ ኢትዮጵያን ሊገዙ ይቻላቸዋል ወይ ነው። በኢትዮጵያ የኃይሎች አሰላለፍ ውስጥ ትልቁን ሚና እየተጫወቱ ያሉት ሦስት ብሔሮች ናቸው። አማራ ትግራዋይና ኦሮሞ። ሲዳማ፣ ወላይታ፣ አፋርና ሶማሌ ክልሎችም አሰርቲቭ እየሆኑ መጥተዋል። ከአማራ በስተቀር ሌሎቹ ማህበረሰቦች አሁን ያሉ ክልሎች እንዲፈርሱ አይፈልጉም። ይልቁንም የክልልነት ደረጃ ያላጉኙት ጥያቄአቸው እንዲመለስ እየገፉ ነው። ለሌሎቹ የማትመች ለአማራ ብቻ የምትመች ኢትዮጵያ ታዲያ ትዘልቃለች ነው ጥያቄው። ከተማ ቀመስ አማሮች በሚቆጣጠሯቸው ሚዲያዎች ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ስለጮሁም መሬት ላይ ያለውን እውነታ ይለውጡታል ማለት ዘበት ነው። እርግጥ ነው ኦሮሞና ትግራይ በቁጥር አነስ ያሉ ሚዲያዎች አሏቸው። በነበረው መዋቅራዊ አድልዎ ምክንያት ሌሎቹ ገና አቅማቸውን አላዳበሩምና ድምፃቸውን በሚዲያ እንደልብ ማሰማት እየቻሉ አይደለም። አንድ ኦ ኤም ኤን ቢኖር እርሱን በአማራ ኤሊቶች ጩሀት ኮሎኔል አብይ አህመድ ዘግቶታል። ይህ ማለት ግን መሬት ላይ ያለው ሃቅ ይለወጣል ማለት አይደለም። በብዛት በሀገር ውስጥም በውጭም የሚንቀሳቀሱ ሚዲያዎችን የያዙት አማሮቸ ናቸው። እነዚህ ሚዲያዎች በዘር ተደራጅተው ነው ሌላውን እያጠቁ ያሉት። የተለየ ድምፅ፣ የተለየ አማራጭ አያስተናግዱም። ክልል ይፍረስ፣ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ችግር ክልሎች ናቸው ይሉናል። መደዴው ጠቅላይ ሚኒስትርም ይህን ጩሀት እውነት ብሎ ተቀብሎ ከማይወጣበት አዘቅት ውስጥ ተዘፍቋል። የርሱ የስልጣን ጉጉትና የነዚህ ኃይሎች ጦረኛ ከበሮ በጋራ ኢትዮጵያን ወደ ሞት እያንደረደራት ነው። ባሻዬ፣ ከእንግዲህ አንድ ብሔር በሌላው ኪሳራ እየተደሰተ ኢትዮጵያን ማስቀጠል አይቻለውም። ለምሳሌ አማራው በኦሮሞ ላይ እያላገጠ፣ እየፈረጀው፣ እያንገላታው፣ እያሰረው ኢትዮጵያን መግዛት አይቻለውም። የኦሮሞን ሚዲያ እየዘጋ፣ ፖለቲከኞቹን በአሸባሪነት እየፈረጀው፣ ዘብጢያ እየወረወራቸው ኢትዮጵያን ሊያክም አይችልም። ይህ ዘዴ ጊዜው አልፎበታል። ትግራይን ደምስስልኝ ወልቃይትን መልስልኝ የሚል በዘር የተደራጀ ኃይል የኢትዮጵያ በሽታ እንጂ የኢትዮጵያ ሀኪም ሊሆን አይችልም። ግምባር ግምባሩን ፈርክስልኝ፣ በደረት ግጠምልኝ የሚል ሞት ጠሪ፣ ቅጠል በጣሽ ደም አፍሳሽ ደብተራ የኢትዮጵያ ደዌ እንጂ ፈውስ አይሆንም ኃይል ጉልበት፣ እብሪት ትናንት ሰርቶ ይሆናል። በ19ኛውና በ20ኛው ክፍለዘመናት እነዚህ ዘዴዎች ሰርተው ነበር። የቂሎች ቂል አብይ አህመድ ይህን ዘዴ ዛሬም ሊተገብረው ይሞክራል። ትንሽ እንኳን መሬት ላይ ያለውን እውነታ የማይረዱ ድንዙዛንን ሰምቶ ወደ መቀመቅ እየሮጠ ነው። በዚህ አያያዝ አብይ የመጨረሻው የኢትዮጵያ መሪ መሆኑን መናገር ነብይነትን አይጠይቅም። በለው በለው ባዮች፣ ምሁርና ዲያቆን መካሪዎች፣ ቅጥር አንጋቾች፣ ሰልፍ ወጪዎች፣ባንድራ ለባሾች የማያዩት ነገር አለ። በአንድ ሳምንት የገበያ አድማ የኢትዮጵያን መንግስት ማንበርከክ የሚችል ቄሮ ጉልበቱን ባለፈው ሰሞን አሳይቷቸዋል። አሁንም ሌላ ዙር ኢኮኖሚያዊ ዕቀባ ሊተገብር ነው። መሪዎቹ ታስረው የሚተኘ ኦሮሞ ካለ እርሱ የሞተ ብቻ ነው። ፊሊሚያው ግልፅ ነው። አማራ ኦሮሞን አንበርክኮ ይገዛል ወይስ አይገዛውም ነው። የህግ የበላይነት ገለመሌ የሚባል የዳቦ ስም ቦታ የለውም። እንከባበር እያልን ነው። እስካሁን አሰላለፉን ያልተረዳ ካለ እርሱ ከኢትዮጵያ ፖለቲካ ውጭ ነው። አንድ ነገር ግልፅ መሆን አለበት። የኦሮሞ ህዝብ የማይፈልገው አገዛዝ ከእንግዲህ ቦታ የለውም። ኦሮሞ ጦርነቱ ከማን ጋር እንደሆነ ገብቶታል። ምን ላይ በማተኮር ታንክና መትረየሱን እንደሚያሸንፍ ያውቃል። ጀዋር፣ በቀለ፣ አብዲ፣ ሽጉጥ፣ ሚካኤል፣ ሃምዛ ባጠቃላይ አስር ሺዎች የኦሮሞዎች ታስረው የምትረጋጋ፣ የምምትታከም ኢትዮጵያ አትኖርም። የአማራ ኤሊት ወይም የዚህ ኤሊት ቅጥረኛ ኦሮሞን እያሰረው፣ እየፈረደበት፣ እያስፈረደበት ኢትዮጵያ ማከም አይቻለውም። ይልቅ እነዚህ የህግ የበላይነት መከበር ኦሮሞ ሲገደል፣ ሲታሰርና ሲገፋ መሆኑ ደስታ እንደሚሰጣቸው ማየት ወገኖች ወደ ህሊናቸው ሊመለሱ ይገባቸዋል። በዚህ ዓይነት በሌላላው ሞትና ስቃይ የሚፈነድቁ ወገኖችን ማየት ያማል። ለኢትዮጵያ የሰከነ ፖለቲካም መንገዱ በጣም ጠባብ መሆኑን ያሳያል። ኢትዮጵያ እንዲትቀጥል ከተፈለገ አዋጩ መንገድ አንድና አንድ ብቻ ነው። ደግሞም እርሱ መንገድ ቀላል ነው። ከማሰርና ከመግደል በላይ ቀላል ነው። የኦሮሞ ፖለቲከኞችን መፍታት፣ ለጠረጴዛ ዙሪያ ዉይይት በሩን በሰፊው መክፈት። ስልጣን ለሽግግር መንግስት ለማስረከብ መዘጋጀት። ኢትዮጵያ ምናልባት የምትታከም ከሆነ በውይይት ብቻ ነው። አለበለዚያ አብይ አህመድ ስሎቮዳን ሜሎሶቪች የመጨረሻው የዩጎዝላቪያ ፕሬዝዳንት እንደሆነ ሁሉ፣ አብይ አህመድም የመጨረሻው የኢትዮጵያ ኤምፓየር ጠቅላይ ሚኒስተር መሆኑ ሳይታለም የተፈታ ነው።

Comments»

1. #OromoProtests Global Solidarity Rally in Saskatoon Rallies for Human Rights in Ethiopia | OromianEconomist - July 25, 2020

[…] የመጨረሻው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስተር? […]

2. Oromo Lawyer Says Protests in Ethiopia Stem From Systematic Discrimination | OromianEconomist - July 28, 2020

[…] የመጨረሻው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስተር? […]


Leave a Reply

Please log in using one of these methods to post your comment:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

%d bloggers like this: