jump to navigation

የቀሩት ምርጫዎች: ኮሎኔል አቢይ ብዙ ችግሮች ዉስጥ ገብቶአል #OromoProtests July 27, 2020

Posted by OromianEconomist in Uncategorized.
Tags: , , , ,
trackback

የቀሩት ምርጫዎች

BY Mekbib Gebeyehu

ኮሎኔል አቢይ ብዙ ችግሮች ዉስጥ ገብቶአል. ችግሮቹ ዘርፈ-ብዙና ስር የሰደዱ ናቸዉ. በኔ ግምት ችግሮቹ ኮሎኔል አቢይ መፍታት ከሚችለዉ በላይ ሄደዋል. የያዜዉ መንድ የጥፋትና ሊሆን የማይችል መሆኑን ቢገነዘብ የብዙ ህይወት ማለፍንና የንብረት መዉደምን መቀነስ ይቻላል.”When you have eliminated the impossible, whatever remains, however improbable, must be the truth”. የሚባል አባባል አለ. ኮሎኔል አቢይ ቢያንስ ሁለት ሊሆኑ የማይችሉትን ከአላማዉ ማሰጣት አለበት. በጥቅሱ እንዳነሳሁት የቀረዉ ምናልባትም ቢሆን እዉነት ይሆናል . ይህ የማይሆነዉን የማስወገድ ዜዴ በምርምር እንዲሁም ለችግሮች መፍትሄ በማምጣት ረገድ ይጠቀሙበታል.ዛሬም ሆነ ወደፊት በዚይች ሃገር የማይሆኑት፡

1. ኢትዮጵያ ዉስጥ አሃዳዊ አስተዳደር በፍጹም ሊመሰረት አይችልም. ሙከራዎች አይደረጉም ማለት አይደለም፣ ግን በፍጹም አይሳካም. ለብዙ ህይወት መጥፋትና ንብረት መዉደም ዋናዉ ምክንያት ሊሆን ይችላላ. የአሃዳዊዉ ስርአት አቀንቃኞች በብዛት ካንድ ብሄር ብቻ የወጡ የፖለቲካ ኤሊቶች መሆናቸዉና ስርአቱ ተሞክሮ የከሸፈ መሆኑ ከምርጫዉ ዉጪ ያደርገዋል. የፈደራል ስርአቱ ድክመት እንዳለ ሆኖ የተለላያዩ ብሄሮች ከፈደራል አስተዳደሩ ያግኙት ጥቅም ለምሳሌ በማንነት፣ በቁዋንቁዋና በባህል አከባቢ አሃዳዊዉን ስርአት እንዳይቀበሉ ያደርጋል. በመሆኑም ያአሃዳዊው ስርአት ሊሆኑ ከማችሉት ዉስጥ የሚመደብ ነዉ. ስርአቱ እንደ ነፍጠኛዉ ስርአት ላለመመለስ ሄዶአል.

2. ኮሎኔል አቢይ አምባገነን ሆኖ ማስተዳደር አይችልም. የህዝቡ ንቃተ ህሊና የደረሰበትና አልገዛም ባይነቱ ጸጥታዉን ለማስጠበቅ አቅም ያሳጣዋል፡ መቆጣጠር ወደ ማይቻልበት ሁኔታ ያደርሰዋል. የኮሎኔሉ ወደ አስመራ ሩጫ ለዚህ ማስረጃ ነዉ. ኤሪትሪያ ደግሞ ብዙ የሚትረዳዉ አይመስለኝም. የአቢይ ለራሱ ጥበቃ ከኢትዮጵያ ይልቅ በኢርትሪያ ጠባቂዎች መተማመን በሌሎች አከባቢ ቅራኔ ያስነሳል. በዉጪ ወታደር እርዳታ አምባገነን መሆን ከባድ ነዉ. የኦሮሚያ ፖሊስ ካለፈዉ የተማረዉ ልምድ አለዉ. ሁኔታዎቹ እየገፉ ሲመጡ ከራሱ ህዝብ ጋር ይሰለፋል. የመከላከያ ሰራዊቱም ቀስ በቀስ ያንኑ ይከተላል. ይህ ብቻ ሳይሆን ኤኮኖሚዉም ለዚህ አመቺ አይደለም. ያለም አቀፉም ህብረተሰብ የኮሎኔሉን ማንነት እየተረዳዉ ነዉ. ብዙ የመገናኛ መሳሪያዎች በሰፊዉ እየዘገቡ ነዉ.ባጭሩ ከላይ ያነሳኋችዉ ሁለት ሁኔታዎች በኢትዮጵያ ፖለቲካ ዉስጥ ሊሆኑ የማይችሉ ናቸዉ. ያንን ስራ ላይ ለማዋል መስራት የጥፋት መንገድ ነዉ. የአማራዉ ኤሊት ይህ ሳይገባዉ ቀርቶ ሳይሆን “ምናልባት ቢሳካ” ከሚል አስተሳሰብ ነዉ. ያን አስተሳሰብ ቢትዉ የበለጠ ይጠቀማሉ.ሊሆኑ የሚችሉት”however improbable”

1. በመፈቃቀድ ላይ የተመሰረተ ብሄር ተኮር ጠንካራ ፈድራሊስም ሊፈጠር ይችላል. ይህ አዝማሚያ በሰፊዉ እየታየ ነዉ. ብዙ ጥናት አዘል ስብሰባዎች እየትካሄዱ ነዉ. የፈደራል ሃይሉ ማለትም ከአምራዉ ኤሊት በስተቀር ሁሉም በዚህ ጎራ ዉስጥ የተሰለፉ ናቸዉ. የተለያዩ ብሄሮች ለምሳሌ የሲዳማ፣ የሃረሪ፣ የትግራይ፣ የቅማንት ወዘት ተወካዮች ትናንት ኦሮም ግሎባል ፎሩም ባካሄደዉ ስብሰባ ላይ የተናገሩት አንዱማስረጃ ነዉ.

2. ኢትዮጵያ የዛሬዉን ቅርጽዋን ታጣለች. ለምሳሌ ትግራይ ወይም ኦሮሚያ ወይም ሁለቱም የራሳቸዉን መንግስት መመስረት ይችላሉ. ለብዙዎቹ ይህ እስኪሆን እዉነት አይመስልም. ሲሆን ግን ለመቀብለ ይገደዳሉ.ይህ የመጀመሪያዉ ሰናሪዮ ካልተሳካ የሚመጣ ነዉ.እንዲዲህ ሊሆኑ የማችሉትን ካስወጣን ሊሆኑ ከሚችሉት ሁለት አማራጮች ጋር ቀርተናል. ማተኮር ያለብን በነሱ ላይ መሆን አልበት. ያንን መረዳት ከላይ ለመንካት እንደሞከርኩት የሚጠፋዉን ህይወትና የሚወድመዉን ንብረት መቀነስ ይቻላል.

Comments»

1. Oromo Lawyer Says Protests in Ethiopia Stem From Systematic Discrimination | OromianEconomist - July 28, 2020

[…] የቀሩት ምርጫዎች: ኮሎኔል አቢይ ብዙ ችግሮች ዉስጥ ገብቶአል&n… […]


Leave a Reply

Please log in using one of these methods to post your comment:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

%d bloggers like this: