jump to navigation

የብልጽግና የሶሻል ሚዲያ ካድሬዎች July 27, 2020

Posted by OromianEconomist in Uncategorized.
trackback

የብልጽግና የሶሻል ሚዲያ ካድሬዎች

By Fatuma Nuryea

የጠ/ሚር አብይ አህመድ አስተዳደር ወደ ስልጣን ከወጣ በሗላ ስራውን የጀመረው የሶሻል ሚዲያዎችን ካድሬዎችን በማደረጀት ነበር።የካድሬ ምልመላውን ስራ የሚሰራው በዛጊ አብርሃ በኩል ነው። ሰንሰለቱ ከሀገር ቤት እስከ ውጭ የሚኖሩ ጋዜጠኞች፣ሚዲያዎች፣ አክቲቪስቶች፣ ተፎካካሪ ተብለው የተመዘገቡ፣ አንድነት ፓርቲዎች እና አቀንቃኞችን ያቀፈ ስብስብ ነው። ወደ ስራ ሲገባ ከጠቅላይ ሚኒስቴር ቢሮ ከፍተኛ በጀት ተመድቦለታል። አንድ የሶሻል ሚዲያ ካድሬ በእያንዳንዷ በሚጽፋት ክፍያ ይፈጸምለታል።”አንድ ካድሬ በዛዲግ አብርሃ በሚመራው ቡድን ምልመላ ሲያደርግ ሀገራችንን እናድን ለሀገር እንሰራ የተጀመረውን የዲሞክራሲ መንገድ ለማስቀጠል ነውጠኞችን መታገል አለብን።” በሚል የካድሬነት ጠመቃ እንደሚደረግለት መረጃውን ካደረሰን ግለሰብ ለማወቅ ተችሏል።በአሁን ወቅት በስደት የሚኖር ኢትዮጵያ ውስጥ በነበረበት ሰአት ብዙ ጊዜ እስር ያገጠመው የተቃዋሚ ፖለቲካ ድርጅ አባል የነበረ ግለሰብ ነበር። የዚህ የሶሻል ሚዲያ ካድሬ ዋና መልማይ የነበረ ሲሆን በአሁን ሰአት ከዚህ ስብስብ ውስጥ እራሱን እንዳገለለ ገልጾልናል።ወደዚህ ስብስብ ሲገባ ኢትዮጵያን ለመታደግ እንስራ በሚል ሲሆን የሱ ስራ የነበረው ከፍተኛ ተከተይ ያላቸውን የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ለዚህ አላማ ማዘጋጀት ነው። በግሉ ብቻ ብዙ ሰዎችን ወደዚህ ስብስብ እንዲገቡ ብዙ ስራ ሰርቷል። ለምሳሌ ስዩም ተሾመ፣ የትነበርክ ታደለ (በኬንያ የሚኖር)፣ ናትናኤል መኮንን ፣ ዮናታን ተስፋዬ፣ ደረጄ ሀ/ወልድ .ወ.ዘ.ተ ከአማራ ብሄርተኞች እስከ የኦሮሞ ብሄርተኞች አቀንቃኝ ነን የሚሉ ይገኙበታል። ከሚዲያዎች እና ከጋዜጠኞች እስከ ከአንድ አፍታ ሚዲያ ፣ ከአባይ ሚዲያ እስከ ኢሳት ዘሀበሻን ጨምሮ እዚህ ስብስብ ውስጥ በዋናነት የተሰለፉ ናቸው።ከነዚህ ሰዎች ውስጥ በሱ ምልመላ የገቡ እንዳሉ ይሄው መረጃ ሰጫቺን ሳይሸሽግ ገልጾልናል። የዚህ አላማ የመጀመሪያ ተመልማዮች የኢሳቶች እና ኢዜማዎች ሰዎች እንደሆኑ ይታወቃል። ጠ/ሚ አብይ አህመድ ለኢሳት 20 ሚሊዮን ብር እንዲሰጣቸው አድርጓል። የኢሳት ጋዘጠኞች ወደ ካድሬነት ጠመቃው ለማስገባት የሚፈልጉትን ግለሰብ ለማማለል ሲፈልጉ ግለሰቡ ባለበት ንጉሱ ጥላሁን ጋር ደውለው እንደሚያወሩ አንዳንዴም ተዋወቁ ብለው እንደሚያስተዋዉቋቸው በዚህ መሰል የማማለል ስትራቴጂ እንደሚጠቀሙ ከኢሳቶች ቅርበት ከነበረው ግለሰብ ለማወቅ ተችሏል።የሶሻል ሚዲያ ካድሬዎች ዋና ስራቸው ምንድነው?የሶሻል ሚዲያ ካድሬዎች ዋና ስራቸው የጠ/ሚሩ እና የብልጽግና ፕሮፓጋንዳ ስራ ይሰራሉ። ተቃዋሚ ናቸው የሚሏቸውን አካላት፣ ታዋቂ ግለሰቦችን፣ ቡድኖችን፣ ፓርቲዎችን፣ ብሄሮችን፣ የሀይማኖት መሪዎችን በህዝቡ እንዲጠሉ እና በጥርጣሬ እንዲታዩ የማድረግ ስራ በዋናነት ይሰራሉ። በተለይ “Ethnic outbidding strategy” በሚባል ስልት አገሪቱን በቀውስ አዙሪት ውስጥ በመድፈቅ፤ ከ”ዘውግ ብሔረተኛ” አደረጃጀት ለመውጣት እንደሚሰሩም ምንጫችን ገልፆልናል!ለምሳሌ ያህል በአብን ፓርቲ፣ በባልደራስ፣ በቄሮ እና በጀዋር ላይ የሚከፈቱት ዘመቻን መጥቀስ ይቻላል። መንግስት የሚፈጽማቸውን ግድያዎች እና የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን ግለሰቦች እና ቡድኖች የፈጸሙት በማስመሰል ትልቅ ዘመቻ ይከፍታሉ። ከማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ እስከ ሰላማዊ ሰልፍ እስከሚደርስ ዘመቻን ያጠቃልላል። በሴኔ 15ቱ የባለስልጣናት ግድያን የአማራ አክቲቪስቶችን እና ፖለቲከኞችን የፈጸሙት ድርጊት አስመስሎ የተከፈተውን ዘመቻ ማስታወስ ይቻላል። በሞጣ ሙስሊሞች ላይ የተፈጸመውን ጥቃት ኡስታዝ አህመዲን እጁ እንዳለበት ተደርጎ የተከፈተው ዘመቻም የዚሁ ስብስብ አንድ አካል ሲሆን የጀዋር መሐመድ የግድያን ሙከራ ውሸት እንደሆነ የተገደሉት 86 ሰዎችን እሱ ያስገደለ እንደሆ ተደርጎ የተከፈቱት የሰም ማጥፋት ዘመቻዎች ይገኙበታል።ስልጠናዎች በምን መልኩ ይሰጣሉ?በጀርመን ሀገር የሚገኝ ጠበቃ እና አስተርጓሚ የሆኑት ዶ/ር ለማ ይፍራሸዋ የተባሉ ግለሰብ በአውሮፖ የሚገኙ የብልጽግና የማህበራዊ ሚዲያ ካድሬዎችን ስልጠና እንደሚሰጣቸው በጀርመን የሚገኙ የናዚ ናሽላሊዝም አቀንቃኞችን ገዢው መንግስት ተጽእኖ ይፈጥራሉ የሚባሉ ሰዎችን በተለያዩ የወንጀል ዶሴዎች በመጥቀስ በክስ እና የሚዲያ ዘመቻ ጫናን ሸሽተው እራሳቸውን እንደሚያገሉ የደረጋል። በተመሳሳይም ይሄን በኢትዮጵያ ለመድገም ተፎካካሪ ተጽእኖ ፈጣሪ የሚባሉትን ግለሰቦችን እና ቡድኖችን ከጀርመን ልምድ በመውሰድ ስልጠና እየሰጠ እንደሚገኙ ከሰልጣኞች መረጃ የደረሰን ሲሆን ወደ ተባሉት ግለሰብም ይሄን ለማረጋገጥ ደውለን ነበር።ስማቸው ዶ/ር ለማ ይፍራሸዋ እንደሚባል። ወደ ጀርመን ከመጡ ሀያ አመት እንደሆናቸው። የራሳቸው የትርጉም ስራ ድርጅት እንዳላቸው። የሶሻል ዲሞክራት አባል መሆናቸውን ገልጸውልናል። “የብልጽግና አባል አይደለሁም። ስለኢትዮጵያ ፖለቲካ ስጠየቅ በመንግስት ሚዲያ ሀሳቤን እገልጻለሁ። እኔ የሰው ልጅ እንዲጠላ የማደርገው ነገር የለም።የሰው ልጅ ተከብሮ ቢኖርበት ሀገር ነው የምኖረው። የሰው ልጅ እንዲጠላ እንዲህ አድርግ ብዬ የምመክርበት ነገር የለኝም። እኔ የህገ መንግስት የአጣሪ ጉባኤ በምርጫ ማራዘም ዙሪያ ላይ ባወጣው ማስታወቂያ ላይ የራሴን አስተያየት ጽፌለሁ። ምርጫው ይራዘም በሚል በሙያዬ የሚሰማኝን ጽፌለሁ። ስልጠና ከመስጠቱ ጋር የሚያገናኘኝ ነገር የለም።” ብለዋል።ይሄን መረጃ ያደረሰን ግለሰብ በበኩሉ የብልጽግ የሶሻል ሚዲያ ካድሬ ስልጠና በጀርመን እና በአዲስ አበባ እንደሚሰጣቸው አረጋግጦልናል።” ወደዚህ ስብስብ ሲገባ አላማው ለሀገር ጉዳይ ነበር። ሀገርን የማዳን እና ለኢትዮጵያ የተሻለ ነገር ለማበርከት ነበር። ውስጡ ገብቼ ስመለከት ግን የሚሰራው ለሀገር ሳይሆን ለስልጣን ብቻ ነው። ስለዚህ የታሰርኩት፣ የተሰደድኩት አምባገነን መንግስት ለመመስረት ሳይሆን ፍትህ የሰፈነባት ኢትዮጵያ እድትመሰረት ነው። ስለዚህ ከዚህ ስብስብ እራሴን አግልያለሁ።” ሲል ገልጾልናል።

Comments»

1. Oromo Lawyer Says Protests in Ethiopia Stem From Systematic Discrimination | OromianEconomist - July 28, 2020

[…] የብልጽግና የሶሻል ሚዲያ ካድሬዎች […]


Leave a Reply

Please log in using one of these methods to post your comment:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

%d bloggers like this: