jump to navigation

KMN: የአርቲስት ሀጫሉ ግድያና የሰባተኛው የኢትዮጵያ ንጉስ ድብቅ ሴራ! July 30, 2020

Posted by OromianEconomist in Uncategorized.
trackback

የአርቲስት ሀጫሉ ግድያና የሰባተኛው የኢትዮጵያ ንጉስ ድብቅ ሴራ!

KMN, July 29/2020

ኦሮሞ በግፍ በተገደለ ቁጥር የመንግስት ባለስልጣናት የሚያንጋጉት የይስሙላ መግለጫ ለኦሮሞ ህዝብ አዲስ አይደለም። የሀጫሉን ግድያ አስመልክቶ ግን የተተወነው ድራማ የኦሮሞ ህዝብን እይታ ሊጋርድ አልቻለም። አብይ እና ግብረ አበሮቹ ነፍጠኞች የዛሬ ዓመት ያገሪቷን ኢታማዦር ሹም ጀነራል ሰዐረ መኮንንና ጓዳቸው የነበሩትን ጀነራል ገዛኢ አበራን፣ ዶ/ር አምባቸው መኮንን እና በፌደራሊዝም የሚያምኑ የአማራ ክልል ብሔርተኛ አመራሮችን በግፍ በመግደል ምርጥ ድራማ ሰርተዋል። ዛሬም በተመሳሳይ አርቲስት ሀጫሉን ቀርጥፈው በልተው ሲያበቁ የህዝብን እይታ ለማዛባት የፈበረኩትን ድራማ ቀድመው ባቀናበሩት መሠረት ለመተወን ሞክረዋል። ሀጫሉን የገደሉት አብይና አሃዳውያን ነፍጠኞች መሆናቸውን ስንናገር በምክንያት ነው። አብይና የምኒልክ ሥርዓት ናፋቂዎች አርቲስት ሀጫሉን የገደሉት ለራሳቸው የፖለቲካ ትርፍ ነው። ተከድኖ የሚቀር ዘላለማዊ ሚስጥር የለም። ጉዳዩ እንዲህ ነው። ጠ/ሚ አብይ አህመድ እና ግብረ አበሮቹ ሀጫሉ ለኦሮሚያ ሚዲያ ኔትዎርክ ቴሌቪዥን የሰጠውን ቃለ መጠይቅ ተመለከቱ። አርቲስቱ በተናገራቸው ንግግሮች በጣም ተበሳጩ። በተለይ ደግሞ ሀጫሉ ወደፊት ”በቅርቡ ለሁሉም ነገር መልስ የሚሆን ሥራ ይዤ ብቅ እላለሁ” ያለውን ንግግር ከሀጫሉ አንደበት ሲሰሙ በድንጋጤ የሚይዙትና የሚጨብጡት ጠፋቸው። ጉዳዩ ከዚህ ቀደም ሀጫሉን ቤተ መንግስት ድረስ ጠርተው ያስጠነቀቁትና ግን ደግሞ የሀጫሉን ቆራጥነት በሚገባ የሚያውቁት ጠ/ሚ አብይ አህመድን በእጅጉ አሳሰባቸው። የዲያብሎስ ዳንኤል ክብረት ግፊትም በእጅጉ በረታባቸው።እናም በዚህ ጉዳይ እንቅልፍ ያጡት ጠቅላይ ወዲያውኑ ደመላሽ ገ/ሚካኤልን ጠርተው አማከሩት። “አርቲስት ሀጫሉ ለኦሮሚያ ሚዲያ ኔትዎርክ ቴሌቪዥን የሰጠውን ቃለ መጠይቅ ተመልክተህዋል? ሀጫሉ እጅግ በጣም አደገኛ አርቲስት ነው። አሁን ደግሞ አደገኛ ስራ እየሰራ ያለ ይመስለኛል። እንደሚታወቀው ይህ ግለሰብ በቄሮ ዘንድም ከፍተኛ ተሰሠሚነት አለው። እስኪጣራ ብለን እንጂ ከኦነግ ሸማቂዎች ጋር ግኑኝነት እንደነበረውም መረጃ ነበረን። ከቃለ መጠይቁ በኋላ በተከናወነው የማጣራት ስራ ደግሞ በዚህ ’ለሁሉም ነገር መልስ የሚሆን’ ባለው አዲስ ስራው የኦሮሞ ቄሮዎች ሸማቂዎችን እንዲቀላቀሉ የሚያነሳሳ መሆኑን ደርሰንበታል። ይህ ግለሰብ በፊንፊኔ ጉዳይ ላይ የሚያራምደው ዋልታ ረገጥ አቋሙም አስቀድመን የምናውቀው ነው። በበኩሌ ይህ ልጅ አሁን ቀዩን መስመር የረገጠ ይመስለኛል። ስለዚህ አስቀድመን አስቸኳይ መፍትሔ ልናበጅለት ይገባል ብዬ አምናለሁ።” አሉት። አክለውም ”በማን ይፈጸም? መቼ? የት? እንዴት? ለሚለው የዕቅዱን ዝርዝር መርሀ ግብር በ24 ሰዓት ጊዜ ውስጥ እንድታጠናቅቅ ይሁን። ከአፈጻጸሙ አስቀድሞ ግን ዝርዝር ዕቅዱን ማወቅ እፈልጋለሁ።” በማለት የግድያ ጠበብቱን አሰናበቱት። ከጉዳዩ ጋር አያይዘው የኦሮሞ ፖለቲከኞችን ለመወንጀል ደግሞ ለአቶ ሽመልስ አብዲሳ እና ለኢንጂነር ታከለ ኡማ ተመሳሳይ ትዕዛዝ ተሰጣቸው።ደመላሽ በተባለው የጊዜ ገደብ እቅዱን አዘጋጅቶ አቀረበላቸው። ጠቅላዩም የሀጫሉን ነፍስ ለመቅጨት የተነደፈውን የጥፋት ዕቅድ አጸደቁት። እንዲተገበርም ጥብቅ ትዕዛዝ አስተላለፉ። በአቶ ደመላሽ መሪነትና በአቶ ዮሀንስ ምትኩ አስፈጻሚነት የቤተ መንግስቱ ልዩ የጥበቃ ኃይል አባል የሆነችው ወታደር ላምሮት ከማልን ልከው የአርቲስት ሀጫሉን ህይወት ቀጠፉ። አቶ ሽመልስ እና ኢንጂነር ታከለም ምርጥ ተዋናይ ሆነው በድራማው ተሳተፉ። ጥቁር ለብሰው ሲያበቁ በሚዲያ ቀርበው የአዞ እንባ አነቡ። ወንጀላቸውንም በቀጥታ ሌሎች ላይ ደፈደፉት። ወንጀላቸውን በካይሮ፣ በወያኔ፣ በኦነግ ሸኔ እና በኦሮሞ ምሁራን ላይ ለመለጠፍ የተውኔቱን ሁለተኛ ምዕራፍ አጧጧፉት። ጀዋር መሀመድን፣ በቀለ ገርባን፣ ሀምዛ ቦረናን…ወዘተ አፍነው በማሰር አርቲስት ሀጫሉ ላይ የፈጸሙትን አሰቃቂ ግፍ ንጹሃኖቹ ወያኔ፣ ኦነግ ሸኔ እና የኦሮሞ ምሁራን ላይ ለማላከክ በብርቱ ተጉ። ጸያፍ ድርጊታቸውንም ከአርቲስቱ አስክሬን ጋር በፍጥነት ከፊንፊኔ አርቀው ለመቅበር ወሰኑ። ለዚህም ነው የሀጫሉ ሬሳ አምቦ ተወስዶ እንዲቀበር ግፊት ከማድረግ አልፈው ማምሻው ላይ አስክሬኑን በሄሊኮፕተር አምቦ ያስገቡት። እዚህ ጋር የኦሮሞ ህዝብ ቆም ብሎ ራሱን መጠየቅ የሚገባው ጥቂት ጥያቄዎች አሉ። ሀጫሉ ለኦሮሚያ ሚዲያ ኔትዎርክ በሰጠው ቃለ መጠይቅ ላይ ነፍጠኞችን ክፉኛ አስቆጥቷል። ብልጽግናን በብርቱ ተችቷል! ታዲያ ሀጫሉ ሲገደል የአማራ ኢሊቶችና የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ለምን አልተጠረጠሩም? የኦሮሞ ፓርቲ አመራሮች ብቻ ለምን ተጠረጠሩ? ለምን እነርሱ ብቻ ታሰሩ? አንድም የነፍጠኞች ሚዲያ ሳይነካ የኦሮሞ ህዝብ ልሳን የሆነው ኦሮሚያ ሚዲያ ኔትዎርክ ብቻ ለምን ተዘጋ? የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትዎርክ ጋዜጠኞች ብቻ ለምን ታገቱ? በዚሁ ቀን የሀጫሉን ሬሳ ለመቀበል የወጡ የኦሮሞ ወጣቶች በመንግስት ወታደሮች ጥይት ሲዘንብባቸው፤ ሲቆስሉና ሲገደሉ፤ ለተጨማሪ የጥፋት ተልዕኮ ተደራጅተው የተሠማሩት የነፍጠኞች የጥፋት ግብረ ሀይሎች ግን ያለማንም ከልካይነትና ሀይ ባይነት የኦቦ ድንቁ ደያሳ ንብረት የሆነውን የሪፍት ቫሊ ዩኒቨርቲ ቅርንጫፎችን በሙሉ ሲዘርፉና ሲያወድሙ የዋሉት እንዴትና በምን ስሌት ነው? ሀጫሉ ሲገደል አጠገቡ የነበረችው ወታደር ላምሮት ከማል የት ገባች? ወ/ሮ አዳነች ሚዲያ ፊት ቆማ ለምን ተንተባተበች? የኦሮሞ ህዝብ እነዚህን ጥያቄዎች ራሱን መጠየቅና ምላሽ ማግኘት ይኖርበታል። ይህ የአብይና የአሃዳውያን ነፍጠኞች ድራማ እነዚህ ሰዎች ለኦሮሞ ህዝብ ያላቸውን ቅጥ ያጣ ጥላቻና ንቀት የሚያመለክት የሴረኝነት ተውኔት ነው። በዚህ ተልካሻ ድራማ ኦሮሞን መሸወድ መቼም አይሳካላቸውም። የኦሮሞ ህዝብ የሀጫሉ ገዳዮች እነማን እንደሆኑ ጠንቅቆ ያውቃል። ይህ ታጋሽ ህዝብ ትናንትም የአርቲት ኤቢሳ አዱኛ ገዳዮችን እያወቀ! የአርቲት ዮሴፍ ገመቹ ገዳዮችን እያወቀ! የአርቲት ኦስማዮ ሙሳ ገዳዮችን እያወቀ! የአርቲስት ዳዲ ገላን ገዳዮችን እያወቀ ታግሶ አብሮ ኖሯል! አርቲስት ሀጫሉም ሰኔ 22/2012 ከምሽቱ 3:30 ሰዓት ላይ ተመሳሳይ ጽዋ ተጎነጨ። ከንግዲህ የኦሮሞ ህዝብ ከልጆቹ ገዳዮች ጋር ታግሶ ለመኖር ትዕግስቱ ተሟጧል! የታሠሩ የኦሮሞ ምሁራን ባስቸኳይ እንዲለቀቁ መራር ትግል ማድረግ አለበት። የሀጫሉን ጨምሮ በግፍ የፈሰሰው የንጹሃን የህዝብ ልጆች ደም በከንቱ ፈሶ አይቀርም። ነገ ሳይሆን ዛሬ! በኦሮሞ ሀዝብ አንድነትና ብርቱ ክንድ ይታፈሳልና!!!ግልጽ መልክዕት! ከኦሮሞ ህዝብ የቁርጥ ቀን ልጆች!ለኦቦ ለማ መገርሳ!በማር አንደበትህ ላታለልከንና ድላችንን ነጥቀህ ለሰባተኛው የኢትዮጵያ ንጉስ ገጸ-በረከት ያበረከትከው ኦቦ ለማ ሆይ! ትናንት በማር አንደበትህ ስትሸነግለን በየዋህነታችን አምነን ተከተልንህ። ”ጌታችን እናንተ ናችሁ! አጥፍተናልና ይቅር በሉን! ልንክሳችሁ ተነስተናልና ጊዜ ስጡን!” ስትለን ወንድማችን ነህ ብለን ያለ ምንም መጠራጠር ድላችንን አስረከብንህ። ዛሬ አንተ አባብለህ በጫንክብን የጭቆና ቋጥኝ ስንጨፈለቅ፣ አንተ በጠመድክብን የግፍ መትረየስ በጅምላ ስንታጨድ፣ ድምጽህን አጥፍተህ በቅምጥል ህይወት ስትቀይረን፣ ምላስህን ውጠህና አንደበትህን ቆልፈህ በስልጣን ጫካ ውስጥ ራስህን ስትሸሽግ ታዘብንህ። ዛሬ ከእኛ ዘንድ ምንም ወቀሳ የለብህም። ነገር ግን አንድ ሀቅ እንጠቁምህ። በሄድክበት ሁሉ የኦሮሞ ሰማዕታት አጥንት ይወጋሃል። ለነጻነታችን የፈሰሰው የኦሮሞ ልጆች ደም አፍ አውጥቶ ይወቅስሃል። ጣዕረ ሞታቸው በሄድክበት ሁሉ ይከተለሃል። ነገ ደግሞ ነፍሳቸው በፈጣሪ ፊት ይወቅስሃል። ፈጣሪ አምላክም በክህደትህ ልክ የማይቀረው ፍትሃዊ ፍርዱን ይሰጥሃል። እናም፣ ኦቦ ለማ ሆይ! ነገ በእውነተኛው ቀን ፈጣሪ ፊት ቀርበን ለመወቃቀስ ያብቃን!!!ግልጽ መልክዕት! ከኦሮሞ ህዝብ የቁርጥ ቀን ልጆች!ለሰባተኛው የኢትዮጵያ ንጉስ! ሰባተኛው የኢትዮጵያ ንጉስ ሆይ! ትናንት በኦሮሞ ልጆች ህይወትና ደም መስዋዕትነት ከባርነት ወደ ነጻነት ተሸጋገርክ። ከሎሌነት ወደ ንጉስነት ተረማመድክ። ከታዛዥነት ወደ አዛዥነት ተወረወርክ። ቀን ሲወጣልህ ያነገሰህን ህዝብ ከዳህና ከግብረ-አበሮችህ ጋር ተወዳጀህ። የነፍጠኞችን አጽም ከመቃብር አስነስተህ ዳግም ቤተ መንግስት አስገባህ። ከዚያም የኦሮሞን ስነ ልቦና በመግደል ዳግም ወደ ባርነት አዘቅት መዶል ተመኘህ። እንደተመኘሀውም ነፍጠኞችን አደራጅተህ የግድያ ግብረ ሀይል ውጪ ሀገር አሰልጥነህ ታዋቂና ቁልፍ የኦሮሞ ልጆች ላይ ስውር የግድያ ዘመቻ ከፈትከ። የኦሮሞ ህዝብ ትግል አርማ የሆነው አርቲስት ሀጫሉን በመግደል የኦሮሞን ቀንድ ለመስበር ሞከርክ። የቀድሞ ጌቶችህ (የትናንቱ ኦፒዲኦ) – አባ ዱላ ገመዳ እና ኩማ ደመቅሳ – የአምቦ አድባር የነበሩት ኦቦ ደራራ ከፈኔ ላይ የፈጸሙትን – የጭካኔ ታሪክ አድሰህ አምቦን ዳግም የሀዘን ማቅ አለበስካት። የኦሮሞ ህዝብን ዓይን ደንቁለህ ብሌኑን አጨለምክ። ልቡን በግፍ አደማህ። በኦሮሞ ህዝብ የደምና የእንባ ጎርፍ ዋኘህ። መግደል ሳያንስህ የሀጫሉን ሬሳ ቀብር ነስተህ አንገላታህ። ከሠፊዋ የፊንፊኔ መሬት ሁለት ክንድ አጥቅ ነፍገህ ሬሳውን አረከስክ። የሀጫሉን ቤተሰቦች በሀዘን አቆራምደህ ጥይት መረቅህላቸው። የሀጫሉን አጎት ገድለህ ተጨማሪ ሬሳ አስታቀፍካቸው። በልጃቸው ሀዘን የተሰበሩትን የሀጫሉ ቤተሰቦች በጥይት ቋንቋ “መጽናናትን” ተመኘህላቸው። ስለ ሀጫሉ ፍትህ ያለቀሱትን፣ ለሰማዕቱ አስክሬን ተገቢውን ክብር የተመኙትን የኦሮሞ ልሂቃን ከርቸሌ ዘጋህባቸው። ጀዋርና ኦቦ በቀለን የመሠሉ ታላላቅ የኦሮሞ ታጋዮችን አፍነህ አዋረድክ። በቆመጥ አስቀጠቀጥክ። ዓይንህን በጨው አጥበህ ስታበቃ በግፍ ያፈሰስከውን የወንድማቸውን (የሀጫሉን) ደም እነርሱ ላይ ለማላከክ ደመ ነፍስህን ላይ ታች መናወዝ ጀመርክ። ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የኦሮሞ ህዝብን ትግል ለማዳፈን ዓይን ያወጣ ቅጥፈትህን አደባባይ አወጣህ። ድፍን ኦሮሚያ ውስጥ ስለሀጫሉ ፍትህ የወጡ ወገኖቹን በጥይት እንደቅጠል አረገፍካቸው። በኦሮሞ ደም እጅህን ታጠብክ። በንጹሃኖች ደም ዙፋንህን ማደላደል ተመኘህ። ለቀናትም ቢሆን ስለትህ ያዘልህ። የልጅነት ህልምህ እውን ሆነልህ። የዕድሜ ልክ ምኞትህ ሰመረልህ። እናም፤ ሰባተኛው የኢትዮጵያ ንጉስ ሆይ! በኦሮሞ ደም ነግሰህ በኦሮሞ ደም በመዋኘትህ እንኳን ደስ ያለህ። በመጨረሻ አንድ አጭር ምክር እናካፍልህ። አንድ ተጨባጭ ሀቅንም እንጠቁምህ። ከንግዲህ አንተ የምትፈጽምበትን ግፍ አሜን ብሎ የሚቀበል፣ የምትደርብለትን የውርደት ሸማ ለብሶ መኖር የሚፈቅድ የኦሮሞ ትውልድ ፍጹም እንደይማኖር ልብ ካለህ ልብ ብለህ አስተውል። እኛ የኦሮሞ ልጆች ለህዝባችን ነጻነት ውድ ህይወታችንን ለመገበር ቅንጣት አናመነታም። ከንግዲህ አንተ የምትጭንብንን የምኒልካውያን የባርነት ቀንበር የሚሸከም ጫንቃ በፍጹም የለንም። አንተ የምትጭንብንን አሳፋሪ ባርነት ከመሸከም ሞት ለእኛ ዘላለማዊ ክብር ነው። ሌላው ቢቀር በጥርሶቻችንና በጥፍሮቻችን እንዋጋለን። አንተ የኦሮሞ ህዝብን በግፍ ለመግደል ዝግጁ እንደሆንክ ሁሉ እኛም ኦሮሞ ሆነን በኦሮሞነታችን ለመሞት እስከ መጨረሻው ቆርጠን ተነስተናል። ይህ ውሳኔያችን አጉል ፉከራ መስሎ ከታየህ በእጅጉ ተሳስተሃል። ማረጋገጫ ካስፈለገህ በተግባር ከማረጋገጥ ይበልጥ አስተማማኝ ማስረጃ የለምና የጥፋት ዕቅድህን ቀጥልበትና ውሳኔያችን ተጨባጭ ሀቅ የመሆኑን እውነታ በተግባር አረጋግጥ። ሰባተኛው የኢትዮጵያ ንጉስ ሆይ! እሳት የጨበጠ ሰራዊት እንደምታሰማራብን እናውቃለን። በህገ አራዊት የሚመራና የኦሮሞ ህዝብ ደም የጠማው አራዊት አሰማርተህ እንደምትጨፈጭፈን እንገነዘባለን። ከሰማይ የምታዘንብብን የእሳት መዓት የሚኖርህ ከሆነ እሱንም ደርበህ አዝምትብን። በዚህ ወቅት ሞት ለእኛ ለቁቤ ትውልድ ሰርግና ምላሽ ነው። አንተ የደገስክልንን አፈናና የጅምላ ሞት እያለቀስን ሳይሆን እየጨፈርን በእልልታ ለመቀበል ቆርጠናል። የቁቤ ትውልድ በህይወት እስካለ ድረስ የኦሮሞ ህዝብን ዳግም ወደ ባርነት አዘቅት ለማንደርደር ከአሃዳውያን ጋር የነደፍከው የጥፋት ዕቅድህ ፈጽሞ ሊሰምር አይችልም። ሰይጣናዊ ዕቅድህ ሊሰምር የሚችለው ሀምሳ ሚሊዮኑን የኦሮሞ ህዝብ በጅምላ መቅበር ስትችል ብቻ ነው። አንተ በምታሰማራብን ደም የጠማው ነፍሰ ገዳይ ሰራዊትህ የሀምሳ ሚልዮን ኦሮሞዎች ግብዓተ መሬት እስኪጠናቀቅ ድረስ የጀመርነው መራር ትግላችን ከቀን ወደ ቀን ይበልጥ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን እነሆ ሰው ሆነን ስንፈጠር ሙሉ ነጻነት አጎናጽፎ በፈጠረን ፈጣሪያችን ስም ቃል እንገባልሃለን። ሽንፈት ለነፈሰ ገዳዮ አብይና ግብረ አበሮቹ! ድል ለሰፊው የኦሮሞ ህዝብ ይሆናል!!!ከኦሮሞ ህዝብ የቁርጥ ቀን ልጆች!ሀምሌ 20/2012 ዓም

Comments»

No comments yet — be the first.

Leave a Reply

Please log in using one of these methods to post your comment:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

%d bloggers like this: