አንተ አልቻልክም: አዎ አንተ አትችልም!በሰይፍ መቅላት፣ረግጦ መግዛት… April 13, 2019
Posted by OromianEconomist in Uncategorized.Tags: #March4Abiy, Abiy Ahmed, Ethiopia's colonizing Structure, Social changes, Team Lemma
1 comment so far
#አንተ_አልቻልክም ::
አዎ አንተ አትችልም!
በሰይፍ መቅላት፣
ረግጦ መግዛት…. አልቻልክም፤
አንተ እጅ መቁረጥ፣
እግር መንሳት.. አልቻልክም፤
ዘር ማጥፋት፣
ደሃን መግፋት…. ፈጽሞውኑ አልቻልክም፤
የኔን ተቀበል ያንተን ወዲያ ጣል፤
በአንተ ወርቅ እኔ ልድመቅ ማለት፤
ምን በወጣህ አንተ አትችልም፤
ስለዚህ አንተ አልቻልክም::
ጀግናን በስቅላት፣ ገሎ ለጅብ መስጠት
40 ምሁር ከወደቁበት አንስቶ ማክበር እንጂ 60 ምሁር ባንዴ መቅበር እንዴት ይቻልሃል? አትችልም!
ለመላው አፍሪካ መስራት እንጂ ምስኪኑን የኤርትራ ህዝብ መውጋት አይሆንልህም::
ማስታረቅ እንጂ ማራራቅ፤
ወንድም ህዝብ ደም ይፍሰስ አትልም!
ስለዚህ አልቻልክም::
የእናቶችን እንባ ማበስ እንጂ የራሔልን እንባ ማፍሰስ፤
የልጅ እሬሳ ላይ አስቀምጦ በሰደፍ አናቷን ማፍረስ፤
አንተ አይሆንልህም አመድ አፋሽ ቢያረጉህም::
የችሎታ ስሌቱ ይሄ ለሆነ ህዝብ አንተ አትችልም::
በቃ አትችልማ!!!
ሞታቸውን የሚጠባበቁትን ከእስር ለቀሃል::
ስለዚህ አልቻልክም:: ምክንያቱም ጀግንነት ለእነሱ መግደል ነዋ!
የተበተኑትን ከአለም ዙርያ ሰብሰበሃል፤
በፍቅር አቅፈህ አብረህ አልቅሰሃል፤
ያለመዱትን? የማያዉቁትን?
ስለሆነም አልቻልክም::
ለአህያ ማር እየሰጠህ አስቸግረሃል፤
አህያ የለመደችው ሳር እንጂ ማር አይጥማትም፤
ስለዚህ ችሎታ ይጎለሃል::
ፒንሳ የልህም፣ የሃይላንድ ዉሃ የለህም፤
የምድር ስር ጉድጓድ፣ጫለማ ቤት የለህም፤
ማስፈራርያ አውሬ የለህም፤
ሽንት የምትሸና የመብራቱ ልጅ የለችህም፤
ታዲያ ችሎታህ ምኑ ጋር ነው???
ሚድያውን ማፈን፣ የባለጌን አፍ መድፈን፤
እጅግ ተስኖሃል:: ስለዚህ አንተ ሳትቀር ባደባባይ ይሰድቡሃል::
ያሻቸውን ይጽፋሉ ይናገራሉ፤ሲሻቸው ይሰለፋሉ፤ ሲሻቸው ይሸልላሉ(አንተምላይ ሳይቀር)
“ሰማይ አይታረስ ንጉስ አይከሰስ ” ሲል ለኖረ ሰው፤
ለገዢዎች የአምልኮ ስግደት ሲሰግድ ለኖረ ህዝብ፤
የአጋዚን ዱላ ለጠገበ ሰውነት ይሄ እንዴት ይሰማሟል???
ስለዚህ አትችልም ይለሃል::
እጅ መንሻ ሲሰጥ ለኖረ ጉቦ ለለመደ፤
ሌባ ይጥፋ ስትል ሀገሩን የካደ፤
ባዕድ ነው ለሱ፣ የችሎታ ማነስ፣ ባህሉን የናደ::
እሱ ችሎት ለኖረው አንተ ምን አነካከህ?
ከባለቤቱ ያወቀ ቡዳ ነው እየሞተ ያገኛታል መተው ነበረብህ::
እኔ ልንገርህ ዶ/ር አብይ አንተ አትችልም!
ብዙ ሚሊዮን ህዝብ መምራት እንጂ ብዙ ሚሊዮን እብድ መንዳት አትችልም!
via OJA
You must be logged in to post a comment.