Ethiopia: የህወሓቶች ገበና ሲጋለጥ፤ እንደ ወራሪ ጦር የዘረፉት መሬት፣ እንደ ጠላት የትም የበተኑት ገንዘብ! (አፈትልኮ የወጣ ሰነድ) December 4, 2018
Posted by OromianEconomist in Uncategorized.Tags: Africa, African conditions, Corruption, CORRUPTION CRACKDOWN, Ethiopia, Ethiopia: TPLF's corruption empire, Meles Zenawi, Political & Economic Corruption, TPLF Corruption empire and Al Amoudi, TPLF tyranny, TPLF's crimes and political scandal, TPLF’s corruption
2 comments
የህወሓት ዘረፋና የመሬት ወረራ የተጀመረው ገና በትግል ላይ ሳለ ነው። በትግል ወቅት በቁጥጥሩ (ምርኮ) ስር የወደቁ ማናቸውንም ዓይነት ንብረትን የመውረስና ወደ ትግራይ ክልል ሰብስቦ የመውሰድ አባዜ ነበረው። ነገር ግን በዚህ መልኩ ተዘርፎ የሚወሰድ ሃብትና ንብረት ለህወሓቶች በቂ ወይም አጥጋቢ ሆኖ ባለመገኘቱ ከቁሳዊ ሃብት ይልቅ የከተማና ለም የሆኑ የእርሻ መሬቶችን መዝረፍ ጀመረ። የመሬትን ዘላቂ ጥቅምና አዋጭነት የተረዱት ህወሓቶች በ1984 መጀመያ አካባቢ በሰሜን ጎንደርና ወሎ ያሉ ለም የእርሻ መሬቶች ያሉበት ሁመራና ራያ በትግራይ ክልል ስር እንዲጠቃለል አደረጉ።
በመቀጠል በደርግ መንግስት ስር ይተዳደሩ የነበሩ የሜካናይዝድ የእርሻ መሬቶችን፣ ማሽኖችን፣ የባንክ ገንዘቦችን፣ በአጠቃላይ በወቅቱ በመንግስት ቁጥጥር የነበሩ ንብረቶችን “በኢንዳውመነት” ስም እንዲመዘገብ አደረጉ። በመቀጠል በተለያዩ የሀገሪቱ ክልሎች የሚገኙ የእርሻ መሬቶችን በኢንቨስትመንት ስም ተቆጣጠሩ። በዚህ መሰረት በጋምቤላንና አፋር ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ፣ አብዛኛው የቤንሻንጉል-ጉሙዝ የእርሻ እና የከተማ መሬቶች፣ በደቡብ ኦሞ የመንግስት እርሻ ቦታዎች፣ የሆቴል እና የመኖሪያ ቦታዎች፣ በመተማና ጎጃም እርሻ ልማቶች፣ እንዲሁም በአዲስ አበባ እና ዙሪያዋ የሚገኙ ጥሩ የኢንቨስትምት እና የማዕድን ቦታዎችን ያለ ተቀናቃኝ በበላይነት ተቆጣጥረዋል።
በዚህ ተግባር የተሰማሩት ሰዎች የአንድ መንደር ተወላጅ የሆኑ የህወሓት አባላት ናቸው። እነዚህ መንደርተኞች በድብቅ መሬት እንዲወስዱ የተደረገው በወቅቱ የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስተር በነበሩት በአቶ መለስ ዜናዊ ትዕዛዝ ነው። አሁንም እየዘረፉና ሃብቱን እያሸሹ ያሉት እነዚህ ሰዎች ናቸው። ይህን ለማረጋገጥ በኢትዮጵያ ልማት ባንክ አማካኝነት ከዋናው መስሪያ ቤት እስከ ቅርንጫፍ የተሠጡ ብድሮችን፣ እንዲሁም በብድር ማስታመሚያና ማገገሚያ ክፍሎች ያሉት ፕሮጀክቶች የእነማን እንደሆኑ በመመርመር እውነታውን መገንዘብ ይቻላል፡፡
You must be logged in to post a comment.