OMN: Turtii Prof Mararaa waliin Tamsaasa Kallattii (Hag 23, 2020) & በማምለጥ ላይ ያለ አዲስ የሀገረ-መንግስት ግንባታ ሙከራ August 23, 2020
Posted by OromianEconomist in Uncategorized.add a comment
በማምለጥ ላይ ያለ አዲስ የሀገረ-መንግስት ግንባታ ሙከራ
መረራ ጉዲና (ፕሮፌሴር)ለብሔራዊ መግባባት ውይይት የቀረበ ጥናት
ነሐሴ 2012/August 2020
አብዛኛዎቹ የሀገራችን የታሪክ ምሁራን የኢትዮጵያ ታሪክ ከክርስቶስ ልደት በፊት፤ በአስረኛው ምዕተ ዓመት የንግስት ሳባ እና የንጉስ ሰለሞን ግንኙነት በሚባለው ጊዜ ይጀምራል ይላሉ፡፡
ይህ ለአንዳንዶቹ የሚታመን ታሪክ ተደርጎ የሚወሰደው፤ ለሌሎች ደግሞ ተረት እንደነበረ የሚነገረው ክስተት የማስመሳያ ትርክቱ የእስራኤል አምላክ የቀባቸው ገዥዎች ተብሎ በሺዎች ለሚቆጠሩ ዓመታት ንጉሦቹ ቅቡልነትን አግኝተውበታል፡፡ በትርክቱም ሀገሪቷን እስከ 1966 ሕዝባዊ አብዮት ድረስ ያለ ብዙ ጭንቀት ገዝተውበታል፡፡
የዛሬይቱ ሰፊዋ ኢትዮጵያ እንደ ሕብረ ብሔራዊ የነገስታት መንግስት (multi-ethnic empire state) የተፈጠረችው በ2ኛው የ19ኛው ክፍለ ዘመን ግማሽ፤ የዘመነ መሳፍንት ከሚባለው ዘመን በኋላ ስለሆነና ዛሬም በጣም ሰፊ ቀውስ ውስጥ የከተተን ታሪካዊ ዳራም ከዚሁ ጊዜ ጀምሮ ስለሆነ፤ ጽሑፌም ከዘመናዊ ኢትዮጵያ መፈጠር ጋር በተፈጠሩ ችግሮች ላይ ያተኩራል፡፡
የዘመነ መሳፍንትን ክስተት በመለወጥ የተጀመረው የዛሬዋን ሰሜናዊ ኢትዮጵያን አንድ የማድረግ ሕልም በግማሽ ምዕተ ዓመት ውስጥ ከሦስት እጥፍ በላይ የሰፋች ኢትዮጵያን መፍጠር ችሎዋል፡፡ ይህ የታሪክ ክስተት የሦስት ምኞቶች ዉጤት ነበር፡፡ እነዚህም፡-
1ኛ/ ተበታትና የነበረችውን የዛሬዋን ሰሜናዊ ኢትዮጵያ ሕዝቦችን ለማሰባሰብ የታለመ ምኞት፣
2ኛ/ የኦሮሞና የሶማሌ ሕዝቦችን ጨምሮ ሰፊውን የደቡብ ክፍል የማስገበር ምኞት፣
3ኛ/ አፍሪካን ለመቀራመት የመጡትን የአውሮፓ ሀገሮች ጋር የመፎካከር ምኞት ነበሩ፡፡
እነዚህን ሦስት ምኞቶች ለማሳካት የመጀመሪያ የሆነውን ሙከራ የጀመሩት እንደሚታውቁት፤ አፄ ቴዎድሮስ ነበሩ፡፡
ቴዎድሮስ ሕልሞቹን ለማሳካት ጠንካራና ሰፊ ሠራዊት ማደራጀት ነበረባቸው፡፡ ለዚህም ሰፊ መሬት የያዙትን ቄሶች መሬት መቀማትና፣ ዘመናዊ መሳሪያን ከክርስቲያን አውሮፓ ለማግኘት ጥረት ማድረግ ነበር፤የአዉሮፓ መሪዎችን ማሳመን ሲያቅታቸው ደግሞ፤ ሙያውን የሌላቸውን አውሮፓዊያንን ሳይቀር በቤተመንግስታቸው ሰብስበው ከባድ የጦር መሳሪያ ውለዱ እስከ ማለት ደርሰዋል፡፡
ይህም ምኞታቸዉ ይሳካ ዘንድ በነበራቸዉ የጦር መሣሪያ የአካባቢ ገዥዎችንም ለማንበርከክ ተንቀሳቅሰዋል፡፡
ቄሶችን ለመግፋት ያደረጉት ሙከራ እግዚአብሔርን የካዱ ንጉሥ ተብሎ ተሰባከባቸዉ፡፡የአውሮፓዊያንን ዘመናዊ መሳሪያ ለማግኘት ገደብ ያለፈ ጉጉታቸው ከእንግሊዘኞች ጋር ያለጊዜ አላተማቸው፡፡
የየአከባቢውን ገዥዎች በጉልበት ለማንበርከክ እጅና አንገት በመቁረጥ የገፉበት ሙከራ ከእንግሊዞች ጋር ለመዋጋት የቁርጥ ቀን ሲመጣ፤ የትግራይ፣ የወሎ፤ የጎጃም፣ የሸዋ፣ የጎንደር ገዥዎች ሁሉም በሚባልበት ደረጃ ካዷቸው፡፡
በአጭሩ የየአከባቢዉ ገዥዎች በእንግሊዞች እጅ መሞታቸውን ሲሰሙ ከማዘን ይልቅ፤ ተገላገልን ያሉ ይመስላል፡፡ ለዚህም ይመስለኛል፤ ዕውቁ የታሪክ ምሑር ፕሮፌሴር ባህሩ ዘውዴ የቴዎድሮስን ሚና በተሻለ የታሪክ ሚዛን ላይ ለማስቀመጥ ሲሞክር፤ “የተወናበዱ የላዉጥ ነቢይ” (confused prophet of change) ያላቸዉ፡፡ በዚህ የቴዎድሮስ የታሪክ ሚና ላይ ብዙ ሰው ልብ የማያደርገውን የታሪክ ማስታወሻ አስቀምጬ ልለፍ፡፡ ይኼውም ቴዎድሮስ በጊዜው ለነበሩ የአውሮፓ ኃያላን መንግስታት በፃፉት ደብዳቤ ውስጥ፤ “አባቶቼ በሰሩት ኃጥአት ምክንያት እግዚአብሔር “ጋሎችን” በሀገሬ ላይ ለቆ፤ እነሱ ጌቶች ሆነው፤ እኛ የእስራኤል ልጆች የነሱ አሽከሮች ሆነን እንኖር ነበር፡፡ አሁን እግዚአብሔር ከትቢያ አንስቶኝ የኢትዮጵያ ንጉስ አድርጎኛል፡፡ እናንተ ከረዳችሁኝ በጋራ እየሩሳሌምንም ነፃ ልናወጣ እንችላለን” ማለታቸዉ ነዉ፡፡ (ትርጉም የኔ ነው)፡፡ እዚህ ላይ ሁለት ነገሮችን ልብ በሉ፡፡ “ጋሎቹ” የሚባሉት በዘመነ መሳፍንት የጎንደርን ቤተመንግስት በበላይነት ሲቆጣጠሩ የነበሩ የየጁ ኦሮሞዎች መሆናቸውና እየሩሳሌም በጊዜው በእስላሞች እጅ የነበረች መሆንዋን ነው፡፡ ከዚህ አንጻር ማስታወስ የሚያስፈልገው ትልቁ ጉዳይ አፄ ቴዎድሮስ የብሔረሰብ (የዘር) ፖለቲካን በግልፅ የተናገሩ የመጀመሪያዉ የኢትዮጵያ መሪ መሆናቸው ነው፡፡
ከቴዎድሮስ ሞት በኋላ ለሦስት ዓመታት በተክለጊዮርግስና ካሣ (አማቾች የነበሩ ይመስለኛል) ከተካሄደው የሥልጣን ትግል ቦኃላ፤ በአሸናፊነት የወጡት አፄ ዮሐንስ (ካሣ ምርጫ) ነበሩ፡፡ አፄ ዮሐንስ ከሀገር ውስጥ ከወሎ፣ ከጎጃም፣ ከጎንደር፣ ከሸዋ ገዥዎች ጋር እየተጋጩ፤ ከውጭ ደግሞ ከጣሊያኖች፣ ከግብፆችና ከሱዳን መሐዲስቶች ጋር ሲዋጉ በመጨረሻ በመሐድስቶች እጅ ወድቋዋል፡፡ በአጭሩ ዮሐንስ ለትግራይ ሊሂቃን የኢትዮጵያ ማዕከል ነበርን፤ የአክሱም ሐቀኛ ወራሾች እኛ ነን የሚለውን የፖለቲካ ስሜት መፍጠር ቢችሉም፤ በኢትዮጵያ የሀገረ-መንግስት ግንባታ ታሪክ ውስጥ የተለየ ሚና መጨወት አልቻሉም፡፡
በማያሻማ ቋንቋ :- የዛሬዋ ኢትዮጵያ በዋናነት የተፈጠረችውና የዛሬው የታሪክ ጣጣችንም በዋናነት የተፈጠረው በአፄ ምኒልክ ነው፡፡ ምኒልክ ንጉሰ ነገስት ዮሐንስን የሱዳን መሐድስቶች እስክገድሉላቸው ድረስ ከአውሮፓ መንግስታት በተለይም፤ ከጣሊያን በገፍ ባገኙት የጦር መሳሪያ እነራስ ጎበና የመሳሰሉ የኦሮሞ የጦር መሪዎችን በመጠቀም በጊዜው ጠንካራ የሚባል ግዙፍ ሠራዊት መገንበት ችሎዋል፡፡ ይዚህንን ግዙፍ ሠራዊትን ከዮሐንስ ጋር በመዋጋት ከማድከም ይልቅ፡- በአንድ በኩል ዮሐንስን እየገበሩ፤ በሌላ በኩል ደግሞ ያኔ የነበረችውን ኢትዮጵያ ሦስት እጅ ዕጥፍ የሆነ ሰፊ ግዛት መፍጠር ችሎዋል፡፡ በዚህም መጀመሪያ ሳይጠቀለሉ የቀሩትን የሸዋ ኦሮሞዎችን ጠቅልለው ያዙ፡፡ ከዚያ እአአ በ1876 ጉራጌን ብዙ ሕይወት ከጠየቀ ጦርነት በኋላ አስገበሩ፡፡ ብዙ ዝርዝር ውስጥ ሳይገባ የምኒልክን የመስፋፋት ጦርነቶች እንደሚከተለው ማጠቃለል ይቻላል፡፡
ይኼውም በምኒልክና ጀኔራሎቹ ብዙ የግዛት መስፋፋት ጦርነቶችን ቢወጉም ሦስቱ ወሳኝ ጦርነቶች ነበሩ፡፡ አንደኛው በምዕራብ በኩል በእማባቦ (ዛሬ ሆሮ ጉዱሩ በሚባለው ላይ በጎበና መሪነት እአአ በ1882 የተዋጉት ጦርነት ነበር፡፡ ይህ ጦርነት ኦሮሞን ጨምሮ የምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦችን ዕድልና የጎጃም መሪዎች ከሸዋ ጋር የነበራቸውን ፉክክር ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የወሰነና የሸዋንም የበላይነት ያረጋገጠ ነበር፡፡
ሌላው የምኒልክ ጦርነት በአርሲ ላይ እአአ በ1886 የተደመደመዉ ነው፡፡ አርሲዎች ከሌሎች የኦሮሞ አከባቢዎች በተለየ መንገድ ለአምስት ዓመታት በጀግንነት ተዋግተዋል፡፡ በመጨረሻም፤ በራሳቸው በምኒልክ በተመራ ጦር የአውሮፓ መሳሪያ በፈጠረው ልዩነት ሊሸንፉ ችለዋል፡፡ ተመሳሳይ የመከላከል ጦርነት እንዳይገጥማቸው ይመስላል፤ ምኒልክ፡- ዛሬ አለ፤ የለም የሚባለውን የአኖሌ ዓይነት የጭካኔ በትር በአርሲዎች ላይ አሳርፈዋል፡፡ እዚህ ላይ ዛሬ እየተነጋገርንበት ላለው የብሔራዊ መግባባት መሳካት፤ የለም ከሚለው አጉል ክርክር ወጥተን የትናንትናውን የታሪክ ቁስላችንን በሚያክም መልኩ እንድናስተካክል መምከርን እወዳለሁ፡፡
ሦስተኛው የምኒልክ ትልቁ ጦርነት አሁንም በእሳቸው የተመራውና እአአ በ1887 የተካሄደው የጨለንቆ ጦርነት ነበር፡፡ የዚህ ጦርነት ውጤት በጊዜው የሀብታሟ የሐረር ከተማ መንግስት (the Harari city-state) ጨምሮ ምስራቅ ኢትዮጵያ ያለ ደረሰኝ ምኒልክ እጅ የገባበት ሁኔታን ፈጥሯል፡፡ ከዚህም በኋላ ከፋን፣ ወላይታን፣ ወዘተ ለመያዝ ብዙ ደም የፈሰሰባቸው ጦርነቶች ነበሩ፡፡
እንደሚባለው፤ በእንግሊዝ ተስፋፊዎችና በምኒልክ ኢትዮጵያ መካከል የመምረጥ ዕድል የገጠማቸው የቦረና ኦሮሞዎች – ማንን ትመርጣላችሁ ሲባሉ፤ የፊታወራሪ ኃብተጊዮርግስ ፊትን አይተው፤ የእኛኑ ፊት የሚመስለው ይሻላል ብለው በሬፍሬንዴም እየሰፋ በመጣው የኢትዮጵያ መንግስታዊ ግዛት ውስጥ የተቀላቀሉበት ሁኔታም እንዳለ ይነገራል፡፡ እአአ በ1889 አፄ ዮሐንስ በመሐድስቶች ሲገደሉ፤ ኦሮሞን ጨምሮ አብዛኛው ደቡብን የተቆጣጠሩት ምኒልክ ለሰሜኑ ወንድም መሪዎች ፈረንጆች እንደሚሉት “ካሮትና ዱላን” ማስመረጥ ብቻ በቂ ነበር፡፡ የሰሜኑ መሪዎች ምርጫም በማያሻማ መንገድ ካሮት ነበር፡፡ ስለ ካሮቱም በግልፅ ቋንቋ ለማስቀመጥ፤ የኦሮሞ አከባቢዎችን ጨምሮ በደቡብ የተገኘውን እጅግ በጣም ሰፊ ግዛት ዉስጥ በታናሽ ወንድምነት ሹማቶችን መቀረመት ነበር፡፡
በብሔራዊ መግባባታችን ውይይት አንፃር በምኒልክ በተፈጠረው ሰፊ አፄያዊ ግዛት ጋር የተፈጠሩ ችግሮችን ወደ ማንሳቱ ልለፍ፡፡
አንደኛው ችግር፤ እላይ እንዳነሳሁኝ፤ በጉልበት የግዛት ፈጠራ ላይ አኖሌን የመሳሰሉ የታሪክ ጠባሳዎች መፈጠራቸው፤ ሁለተኛውና ዋናው ነገር ግን ከማቅናቱ ጋር የተፈጠረው የፖለቲካል ኤኮኖሚው ነው፡፡ ይህም በነፍጥ ላይ የተመሰረተዉ የፖለቲካ ኤኮኖሚ ዛሬም እያወዛገበን ያለው የነፍጠኛ ሥርአት በሚባለው ላይ የተመሰረተዉ ነዉ፡፡ ለማቅናት የተሰማራው የፊውዳሉ ሥርአት ሰራዊት የገባር ሕዝቦችን ነፃነት ቀምተዋል፡፡ መሬታቸዉን ዘርፈዋል፡፡ ሕዝቦችን በገዛ መሬታቸው ላይ ጭሰኛና አሽከር አድርገዋል፡፡ ቋንቋቸውን አፍነው “በስማ በለው” ገዝቶቸዋል፡፡ በአጭሩ እጅግ በጣም ዘግናኝና ጨካኝ የሆነ የፖለቲካ ሥርአት ጭነውባቸዋል፡፡ አንዳንዱ ነፍጠኛ በሃያ ሺዎች የሚቆጠር ጋሻ መሬትም ነበረው፡፡ ወረ-ገኑ የመሰሰሉ የቤተመንግሥት መሬቶች እጅግ ባጠም ብዙ ነበሩ፡፡ እዚህ ላይ ማስታወስ የሚያስፈልገው የሰሜንና የደቡብ ኢትዮጵያ የመሬት ይዞታም በፍጹም የተለያዩ መሆናቸው ነው፡፡ አነሰም በዛ የሰሜኑ ገበሬ የዘር ግንዱን ቆጥሮ መሬት ያገኛል፡፡ መሬት አያያዙም የወል ነበር፡፡ ሌላው ቢቀር የሚገዛውም በራሱ ቋንቋ ነበር፡፡ በደቡቡ ያለው ግን የመሬት ሥርቱ የግል ሆኖ፤ ጭሰኝነት እጅግ የተንሰራፋበት ነበር፡፡ ሲሶ ለነጋሽ፣ ሲሶ ለቀዳሽ፤ ሲሶ ለአራሽ የሚባለው የኢትዮጵያ ነገስታት የመሬት ፖሊሲ እጅግ በጣም ዘግናኝ በሆነ ሁኔታ ሥራ ላይ የዋለው በደቡቡ የአገራችን ክፍል ላይ ነው፡፡ በ1960ዎቹ የኢትዮጵያ ተማሪዎች ንቅናቄ ዘመን “መሬት ላራሹና የብሔረሰቦች እኩልነት” የተባሉ ሕዝባዊ መፈክሮች የተወለዱት ከዚሁ ጨቋኝ ሥርአት ነበር፡፡ ዛሬ የታሪክ ክለሳ ውስጥ ብንገባም፤ በዕውነቱ ከሁሉም የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብራክ የወጡ ወጣቶች፤ እንዳውም በወቅቱ አማራ ከሚባለው ክፍል የሚበዙ ይመስለኛል፤ መፈክሮቹን በጋራ አስተጋብተዋል፡፡ ለማንኛውም ከብሔራዊ መግባባታችን አንፃር አንድ ነገር ግልፅ ላድርግ፡፡
በ1960ዎቹ የኢትዮጵያ ተማሪዎች ንቅናቄ ዘመን “መሬት ላራሹና የብሔረሰቦች እኩልነት” የተባሉ ሕዝባዊ መፈክሮች የተወለዱት ከዚሁ ጨቋኝ ሥርአት ነበር፡፡ ዛሬ የታሪክ ክለሳ ውስጥ ብንገባም፤ በዕውነቱ ከሁሉም የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብራክ የወጡ ወጣቶች፤ እንዳውም በወቅቱ አማራ ከሚባለው ክፍል የሚበዙ ይመስለኛል፤ መፈክሮቹን በጋራ አስተጋብተዋል፡፡
ለማንኛውም ከብሔራዊ መግባባታችን አንፃር አንድ ነገር ግልፅ ላድርግ፡፡ ነፍጠኛ የሚባለው ሥርአት ገዝፎ የነበረ ሥርአት መሆኑና፤ ይህም ሥርአት ከደቡቡ አርሶ አደር የተሻለ ኑሮ የማይኖሩትን፤ ቢፈልጉ እንኳን የደቡቡን ገበሬ ለመዝረፍ አቅሙም ሆነ ዕድሉን ያልነበራቸውን የአማራ አርሶ-አደርን አይጨምርም፡፡መጨመሩም ጩቡ ነው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ዘሬ አንዳንድ የአማራ ሊሂቃን “እኔም ነፍጠኛ ነኝ” የሚለውን መፈክር ሲያሰሙ፤ ጥቅሙ ኦሮሞን ጨምሮ የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦችን ከአማራ ሕዝብ ጋር ከማጋጨት የዘለለ የፖለቲካ ትርፍ የሚኖረው አይመስለኝም፡፡ ስለሆነም የምንችለውን ያክል ሁላችንም ከሁለቱም ጩቡዎች እንጠንቀቅ ዘንድ አደራ እላለሁ፡፡
ወደ ሌሎች ነጥቦች ከማለፌ በፊት በዋናናት በምኒልክ የተፈጠረችዉ ኢትዮጵያን ለማስተካከል ያቃታቸዉና መሪዎች ማለፍ ያልቻሉት የታሪክ ፈተና ምንድን ነው? የሚለውን ጥያቄ በንፅፅር እንደ ታሪክ ቁጭት ማንሳትን እወዳለሁ፡፡ አፄ ቴዎድሮስ የሞቱት እአአ በ1868 ነበር፡፡ ጃፓንን ከታላላቅ የዓለም መንግስታት ተርታ ያሰለፉአት ማጅ የሚባሉ የንጉሳዊያን ቤተሰብ ወደ ሥልጣን የተመለሱት (The Meiji Restoration) በዚሁ ዓመተ ምህረት ነበር፡፡ የጃፓን ንጉሳዊ ቤተሰቦች በሰላሳ ዓመታት ውስጥ በኤኮኖሚ የበለፀገች ታላቋ ጃፓንን ፈጠሩ፡፡ የጃፓኖች የሀገር ፍቅር ግንባተቻውም ባዶ አልነበረም፡፡ ትዝ እስከሚለኝ ድረስ አንድ የጃፓን ወታደር፤ ንጉሤ የጃፓንን በሁለተኛው የዓለም ጦርነት መሸነፍ አልነገሩኝም ብሎ ከሃምሳ ዓመታት በኋላ በፊሊፕንስ ይሁን፤ በኢንዲኔዢያ ጫካ ውስጥ ተገኝቷል፡፡ ለሀገር ፍቅር ሲባል እራስን በራስ መጥፋት በሁለተኛው የዓለም ጦርነት በትናንሽ አይሮፕላኖችን የአሜሪካን መርከቦች ውሰጥ እየጠለቁ አጥፍቶ መጥፋትን የጀመሩት የጃፓን ካሚከዞች የሚበሉ ነበሩ፡፡ የኢትዮጵያ መሪዎች ግን በተመሳሳይ ጊዜ (እአአ1868-1900) ድረስ ሀገሪቷን ከዓለም ጭራነት አላላቀቋትም፡፡ በነገራችን ላይ ጃፓንና ኢትዮጵያ በ1868 ላይ ተመሳሳይ የዕድገት ደረጃ ላይ ነበሩ፡፡ሌላው ንፅፅሬና የታሪክ ቁጭታችን መሆን ያለበት፤ ታላቋ ጀርመንን የፈጠሩት ቢስማርክና ምኒልክ የአንድ ዘመን ሰዎች ነበሩ፡፡ ምንም ይሁን ምን፤ እነ ቢስማርክ ዓለምን ሁለት ጊዜ ጦርነት ውስጥ መክተት የቻለች ኃያሏን ጀርመን ሲፈጥሩ፤ የኢትዮጵያ ገዥዎች ግን ኋላቀር ኢትዮጵያን ትተውልን ሄደዋል፡፡ በነገራችን ላይ፤ ሀገር ትፈርሳለች ተብሎ ስለተሰጋ፤ የምኒልክ ሞት ለሕዝብ ይፋ የሆነው ከዓመታት በኋላ ነበር ይበላል፡፡በአጠቃላይ ከብሔራዊ መግባባት ፈጠራችን አንፃር መረሳት የሌለበት ቁመነገር፤ በምኒልክና ጣይቱ የተመራው የአድዋው የጋራ ድል እንኳ ያልፈቱት የሚጋጩ ሦስት አመለካከቶች ዛሬም ከኛ ጋር መኖራቸዉ ነዉ፡፡
አንደኛው፤ የሀገራችን ሀገረ-መንግሰት ግንባታ፣ አንድ የነበሩና የተበታተኑ ሕዝቦችን አንድ ላይ መልሶ ያመጣ ነዉ የሚላዉ አመላካከት (reunification)፤
ሁለተኛው፤ በአንድ ላይ ያልነበሩ ሕዝቦችን ወደ አንድ ማምጣት ነዉ የሚለዉ አመላካከት (unification and/or expansion)፤
ሦስተኛው፤ ነፃ ሕዝቦችን ጨፍልቆ በኃይል ማቅናት ነዉ የሚላዉ አመላካከት (colonial thesis) ነቸው፡፡ የበለጠ ግልፅ ለማድረግ፤ የኢትዮጵያ አንድነት አጥባቂዎች ነን የሚሉ፤ በዋናነት የምኒልክን ኃጥያቶች አይቀበሉም፡፡ እንደሚሉት እምዬ ምኒልክ በዓለም ከተደረጉት የሀገር ግንባታዎች ምን የተለየ ነገር ሰራ የሚለውን ሐሳብ ያራምዳሉ፡፡ ከዚያም አልፈዉ ምኒልክ የሠራዉ ሥራ ተላይተዉ የነበሩትን የኢትዮጵያ ግዛቶችን መመለሰ ነበር ይላሉ፡፡ በአንፃሩ የኢትዮጵያ አንድነትን የማያጠብቁ ብሔረተኞች ደግሞ፤ የአቶ ሌንጮ ለታን አባባል ለመጠቀም (አሁን አቋማቸዉ ያ መሆኑን አላዉቅም)፤ ሲያንስ “ኢትዮጵያዊ ለመሆን እንደራደራለን”፤ ሲበዛ ደግሞ ነፃ መንግስታትን እስከ መፍጠር ድረስ እንሄደለን የሚሉ ናቸው፡፡በጥቅሉ እነዚህ አመለካከቶች በፖለቲካችን ለሚጋጩ ሕልሞቻችን መሠረት የሆኑና ካልተገደቡ የሥልጣን ሕልሞች ጋር ተደምሮ የብሔራዊ መግባባት ጥረታችንን የሚያወሳስቡ አመለካከቶች መሆናቸውን በውል መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡
በነምኒልክ የተፈጠረችዉን ኢትዮጵያን ለማስተካከል የተደረጉ ሙከራዎችና ያመለጡን ዕድሎች፡
-1) የልጅ እያሱ ሙከራ፡- ልጅ እያሱ የምኒልክ ልጅ ልጅ ሲሆን፤ በእኩልነት ላይ የተመሰረተች ኢትዮጵያን ለመፍጠር ልዩ ዕድል የነበረውና ያንንም ልዩ ዕድል አውቀው ለመጠቀም ሲሞክር በወጣትነት ዕድሜው ላይ የተቀጨ መሪ ነበር፡፡ በብሔር ግንዱ ኦሮሞና አማራ የነበረ፤ በሃይማኖት ጀርባዉ ክርስቲያንና ሙስሊም የነበረ ሰዉ ነዉ፡፡ ከወሎም በመወለዱ፤ ትግራይንና ሸዋን ለማገናኘት የተሸለ ድልድይ ለመሆን ይችል ነበር፡፡ የሚገርመው ግን የልጅ ኢያሱ ወንጀሎች የሚመነጩት እነዚህኑ አዎንታዊ እሴቶችን ለሀገረ-መንግስት ግንባታ ለመጠቀም መሞከሩ ነበር፡፡ ለምሳሌ አንዳንድ የታሪክ ማሰታወሸዎች እንደሚያስረዱት፤ አርሲዎች እንደልጃቸው ይመለከቱት ነበር ይባላል፡፡ ከሱማሌዎችና ከአፋሮች ጋር ጥብቅ ግንኙነት እንደነበረው በቂ የሆነ የታሪክ ማስረጃ አለ፡፡ ከጎጃሙ ራስ ኃይሉና ከወለጋው ደጃዝማች ጆቴ ቱሉ ጋር የጋብቻ ዝምድና እንደነበረው ይታወቃል፡፡ ቤተክርስቲያንን ለማሰራት የሚጥረውን ያክል (ለምሳሌ የቀጨኔውን መድሐኔ ዓለምን እሱ ነው ያሰራው ይባላል) መስግዶችን ያሰራ ነበር፡፡ ከሥልጣን ላወረዱት የሸዋ ሊሂቃን ግን፤ አንዱና ትልቁ የልጅ ኢያሱ ወንጀል መስጊዶችን ማሰራቱ ነበር፡፡ የመጨረሻው ትልቁ ወንጀል ደግሞ ኢትዮጵያን ለመቀራመት ያንዣበቡ የቅኝ ገዥ ኃይሎች ከሰሜንና ምስራቅ ጣሊያን፣ በምዕራብ፣ በደቡብና በምስራቅ እንግሊዝ፣ በምስራቅ ፈረንሳይ የሦስትዮሽ ስምምነት (tripartite treaty) የሚባለውን እአአ በ1903 ፈርሞ የምኒልክን ሞት ይጠብቁ ከነበሩት መራቅና በአንደኛው የዓለም ጦርነት በአከባቢያችን ግዛት ካልነበራቸው ከነ ጀርመንና ቱርክ ጋር ለመደጋገፍ መሞከሩ ነበር፡፡ በጥቅሉ ከሁሉም በላይ ወንጀሎቹ ሰፊዋን ኢትዮጵያን የፈጠርን እኛ ነን የሚሉትን የሸዋ ሊሂቃንን መጋፋቱ ነበር፡፡ በግልፅ ቋንቋ ለማስቀመጥ – የኢያሱ ወንጀሎች የሸዋ ልጅ አለመሆኑ (የኢያሱ አባት ወሎ ነው)፣ ሐቀኛ የክርስቲያን ልጅ አለመሆኑ (አባቱ የግድ ክርስቲያን ከመሆናቸው በፊት መሐመድ ዓሊ ነበሩና) እንዲሁም የአውሮፓ የቅኝ ገዥ ኃይሎችን ማስቀየሙ ናቸው፡፡ እአአ በ1916፤ በመስቀል ቀን ኢያሱን ለማውረድ ሁሉም መሳሪያዎቻቸውን ይዘው ተሰለፉ፡፡ ቄሶቹ ኢያሱ ሐቀኛ የክርስቲያን ልጅ አይደለም በማለት በማውገዝ፤ የሸዋ ሊሂቃን ሠራዊታቸውን በመሳለፍ፤ የአውሮፓዊያኑ መንግስታት ምክርና ጥበባቸውን ይዘው ተሰለፉ፡፡ የአውሮፓዊያኑ ጥበብ የሚገርም ነበር፤ ኢያሱ በኢትዮጵያ ባንድራ ላይ የእስልምና ምልክት የሆነውን ግማሽ ጨረቃ ለጥፎ ለቱርኮች ዲፕሎማት ሲሰጥ የሚያሳይ ፎቶ ሾፕ የሆነ ሥዕል (ፎቶ ሾፕም፤ የባንድራ ፖለቲካም በልጅ ኢያሱ ዘመንም ነበር) መፈንቅለ መንግስት እንድያከሄዱ የሸዋ ሊሂቃንን መርደት ነበር፡፡ እዚህ ላይ ለታሪክ ትዝብት አንድ ነገር ልብ በሉልኝ፡፡ በአዲስ አበባ ዩኒቬርሲቲ የኢትዮጵያን ፖለቲካ ሳስተምር፤ የሀገረ-መንግስት ግንባታ ችግሮቻችንን በሚመለከት ፈተናም ፈትኜበታለሁ፤ የሸዋው ጦር መሪ የነበሩት ፊታወራሪ ሀብተጊዮርግስ ድናግዴ፤ የመፈንቅለ መንግስቱም መሪ ነበሩ፤ ልጅ ኢያሱን ሲያወርዱ ባስተላለፉት መልዕክት ውስጥ የሚከተለው ይገኝበታል፡፡ “He claims that he eats flesh of cattle slain by Muslims in order to extend frontiers and to win hearts. But these Somali and Muslims have already been brought to heel [and do not need such diplomacy] በጥሬው ሲተረጎም፤ ግዛትን ለማስፋፋትና ልቦችን ለማሰብ ብዬ በሙስልማን የታረደውን የከብት ሥጋ እባላለሁ ይላል፡፡ ነገር ግን እነዚህን ሱማሌዎችና ሙስሊሞችን ቀድሞውኑ ስላንበረከክን እንዲህ ዓይነቱ ዲፕሎማሲ አያስፈልጋቸውም፡፡ይህንን የሀብተጊዮርግስን ንግግር በሚመለከት ሰፊውን ትንተና ለናንተ ትቼ፤ በዚህ ዓይነት የተዛባ አመለካከት ላይ የተገነባችውን ኢትዮጵያን አስተካክሎ በሰፊ መሠረት ላይ የተገነባችውን ኢትዮጵያን ለመፍጠር የተደረገው የመጀመሪያ ሙከራ፤ ልጅ ኢያሱን ለሥልጣን ተብሎ በተጠነሰሰው ሤራ መውረዱን እንዳትረሱት አደራ ማለት እፈልጋለሁ፡፡ ያመለጠንን ዕድል ትርጉም ግን ለታሪክ መተውን አመርጣለሁ፡፡
2. ኢያሱን በወሳኝነት የተኩት ንጉስ ኃይለ ሥላሴ፤ የአገራችንን ሀገረ-መንግስት ግንባታን በተሻለ መሠረት ላይ ለመገንባት ረጅም ጊዜ (ለ60 ዓመታት ገደማ አገሪቷን መርተዋል) በልጅነታቸው የተሻለ የፈረንጅ ዕውቀት የቀመሱና ከማንም የበለጠ ተደጋጋሚ ዕድል ያገኙ ነበሩ፡፡ ነገር ግን በእኔ ግምት፤ ታሪክ የሰጠቸዉን ዕድል አልተጠቃሙበትም፡፡ ንጉስ ኃይለ ሥላሴን የተለያዩ ሰዎች በተለያዩ የታሪክ ሚዛን ላይ ቢያስቀጣቸውምና እኔም ቢሆን በዘመናዊ ትምህርትና በመሳሰሉት ላይ የነበራቸውን አሻራ ቀላል ነው ብዬ ባላስብም፤ ንጉሱ ሕይወት ዘመናቸውን በሙሉ የግል ዝናንና ሥልጣንን ማዕከል ማድረጋቸው ኢትዮጵያዉያንን የ20ኛው ክፍለ ዘመን ሕዝቦች ማድረግ አልተቻላቸውም፡፡ ስለዘር ግንዳቸው ሀሜቱ እንዳለ ሆኖ፤ ከኢያሱ በተሻለ ደረጃ ኦሮሞም፣ ጉራጌም አማራም ነበሩ፡፡ ይህንን ስሬ ግንድ አልተጠቀሙም፡፡ በተለይ ኦሮሞ ከሚባል ሕዝብ ሲሸሹ እንደኖሩ ብዙ ማስረጃዎች አሉ፡፡ ለማንኛዉም፤ አንድንድ ወሳኝ ነገሮችን እንመልከት፡፡ አምቦ 2ኛ ደረጃ ተማሪ በነበርኩበት ጊዜ የሰማሁኝ ይመስለኛል፤ አንድ ጋዜጠኛ ካነበቡት መጽሐፍት ዉስጥ የትኛውን እንደሚያደንቁ ሲጠይቃቸው፤ ቀልባቸውን በጣም የሳበውና ብዙ ጊዜ ደጋግመው ያነበቡት በኒኮሎ ማኪያቬሊ የተፃፈውን “The Prince” የተባለውን እንደነበረ ትዝ ይለኛል፡፡ ንጉሱ አብዘኛዉን የሕይወት ዘመናቸዉን የተመሩት በማኪያቬሊ ምክር ነበር ብዬ እጠረጥራለሁ፡፡ በማክያቬሊ ትምህርት በመመራትም፤ የሥልጣን ተቀናቃኞቻቸውን አንድ በአንድ አስወግደው ከአስራ አራት ዓመታት በኋላ እአአ በ1930 ጥቁር ማክያቬሊ ፈላጭ ቆራጭ ንጉስ ሆነው ወጡ፡፡ እንደ ሀብተጊዮርግስ ዓይነቱን እግዚአብሔር በጊዜ ሲገላገልላቸው፤እንዳ ጎንደሩ ራስ ጉግሳና ባለቤታቸው፤ ንግስት ዘዉድቱን ያስወገዱበት የፖለቲካ ጥበብ፤ በጊዜው በርግጥም አስደናቂ ነበር፡፡ ይህ የንጉሱ ጥበብ፤ አርባ ዓመታትን ቆጥራ የአድዋን ሽንፈት ለመበቀል የመጣቸውን ጣሊያንን ለመከላከል አልረደም፡፡ መንግስታቸዉንም፤ ሀገሪቷንም ለክፉ ቀን አላዘጋጁም፡፡ አድዋ ላይ ታሪካዊ ድል ያስገኙ ጀግኖችም የሉም፡፡ አንድ ለታሪክ የተረፉት ደጀዝማች ባልቻ ሣፎም በንጉሱ ዉሰኔ እስር ቤት ነበሩ፡፡ እዚህም ላይ አንድ የታሪክ ትዝብት አስቀምጬ ማለፍ እፈልጋለሁ፡፡ ኃይለ ሥላሴ ለሥልጣናቸዉ ብሎ የገፉአቸው ብዙ የአከባቢ መሪዎች፤ ከትግራዩ ደጃዝማች ኃይለሥላሴ ጉግሳ ጀምሮ የጎንደር፣ የጎጃም፣ የሸዋ፣ የጅማ፣ የወለጋ ገዥዎች የጣሊያን ባንዳ ሆኑ፡፡ ከሚታወቁት ውስጥ፤ ለታሪክ ተፈሪ ሌላ፤ ሀገር ሌላ ብለው ሲዋጉ የሞቱት ደጃዝማች ባልቻ ብቻ ነበሩ፡፡ በንጉሱ ስህተት ሀገሪቷ ውድ ዋጋ ከፍላለች፡፡ ለዚህ ነው ጠቅላይ ሚኒስቴሩን ጨምሮ የብልፅግና ፓርቲ ባለሥልጣናት ጥዋትና ማታ ባንዳ፣ ባንዳ ሲሉ፤ ግብፅ ሱዳንን ይዛ የምር ከመጣች፤ ሰው ያላሰበውን አሳስበው ለኪሳራ እንዳይዳርጉን የሚፈራው፡፡ ያም ሆነ ይህ፤ ኃይለ ሥላሴ ለጦርነት ያላዘጋጇትን ሀገር በክፉ ቀን ጥለው ሸሹ፡፡ ሐረርጌ ላይም የጂቡቲን ባቡር ሲሳፈሩ ከጦር ሜዳ መሸሻቸውን ለመሸፈን፤ የት ይሄደሉ ብሎ ለጠያቀቸዉ የፈንሳይ ጋዜጠኛ፡ Je ne Suis Pas Soldat (ወታደር አይደለሁም) ብለው ያለፉት፡፡ ለሳቸዉም ፍሕታዊ ለመሆን፤ የአውሮፓ ዲፕሎማቶች ቢከዱአቸውም በዓለም መንግስታት ማህባር ላይ የሚያስመካ ሥራ ሰርተዋል፡፡ ü ሆኖም ከጦር ሜዳ የመሸሻቸው ጉዳይ እስከ መንግስታቸው ፍፃሜ ድረስ እንደ ጥቁር ነጥብ ስትከታላቸዉ ኖራለች፡፡ የአርበኞችም ሆነ የኢትዮጵያ ተማሪዎች ንቅናቄ ዋናው የተቃውሞ መፈክርም ይህች የሽሸት ጉዳይ ነበረች፡፡ከጣሊያን ወረራ በኋላም ንጉስ ኃይለ ሥላሴ በሁለት መሠረታዊ ነገሮች ምክንያት፤ ጋዜጣቸውን አዲስ ዘመን ብለው እንደሰየሙ:- በእርግጥም አዲስ ዘመን፤ ለአዲስቷ ኢትዮጵያ ይፈጠራሉ ብሎ የጠበቁ ብዙ መሆናቸውን ብሎ መገመት አስቸጋሪ አይመስለኝም፡፡ ለአምስት ዓመታት በእንግሊዝ ሀገር በስደት ሲኖሩ፤ ስለራሳቸው ስህተትም ሆነ የሰለጠነው ዓለም ንጉሶች፤ እንዴት ሕዝቦቻቸውን እንደሚመሩና በዛም ምክንያት በሕዝቦቻቸው ዘንድ ተከብረው እንዴት እንደሚኖሩ ተምረዋል ብሎ መጠበቅ ይቻል ነበር፡፡ ከሁሉም በላይ በጣሊያን ወረራ ምክንያት እሳቸውንም ሆነ አገራቸውን ከገጠመው ውርደትና ኪሳራ ይማራሉ ተብሎ ይጠበቅም ነበር፡፡ ከሁሉም አልተማሩም፡፡ በባሰ ሁኔታነና ፍጥነት ወደ ድሮአቸው ተመለሱ፡፡ ለአቢነት፤ አስተዳደራቸውን የተቃወሙ የራያ ገበሬዎችን (ቀዳማይ ወያኔ የሚበለዉ ነዉ) ከየመን በመጡ የእንግሊዝ አይሮፕላኖች አስደበደቡ፡፡ የሪፑቢሊካን አስተሳሰብ ነበራቸው የሚባሉትን አርበኛ ደጃዝማች ታከለን አሰሩ፡፡ እኚህ ሰው ከተደጋጋሚ እስር በኋላ በመጨረሻም ሊይዙአቸው ከተላኩ የንጉሱ ወታደሮች ጋር ሲዋጉ ሞቱ፡፡ ሌላው ስማጥር አርበኛ የነበሩ በላይ ዘለቀንም ያለርህራሄ ሰቀሉ፡፡ የአምባሳደር ብርሃኑ ድንቄ ግልፅ ደብዳቤ እንኳን (አምበሰደር ብርሃኑ፤ በአሜሪካ አምበሰዳር የነበሩና ንጉሱ የገፉበት መንገድ፤ ዉሎ አድሮ ንጉሱንም ሆነ ሀገሪትዋን ለዉርደት እንደሚያበቃ የመጀመሪያ የማስጠንቃቂያ ደወል በአደባባይ የሰጡ በላስልጠን ነበሩ)፣ አሰራራቸውን አላሰለወጠቸዉም፡፡ በፖለቲካ ሥርአታቸው ላይ በተከታታይ ቦንቦች ፈነዱ፡፡ የመጀመሪያዉ ትልቁ ቦንብ በራሳቸው ቤተመንግስት ውስጥ የፈነዳው የነመንግስቱ ንዋይ፤ ያውም የእሳቸውን ክብርና ሞገስ ለመጠበቅ ከፈጠሩት የክብር ዘበኛ ጦር ነበር፡፡ ንጉሱ ከክስተቱ ከመማር ይልቅ ጀኔራል መንግስቱ ናዋይን በሞት ቀጡ፤ የታናሽ ወንድማቸውን ሬሳ፤ እኔን ያየህ ተቀጣ በሚመስል መንገድ በስቅላት ቀጡ፡፡ የበሉበትን ሰባሪዎች ናቸው ብለውም በአዝማሪ አዘለፏቸው፡፡ማን እንደመከራቸው ባይታወቅም ትልቁን የመንግስታቸውን የዲፕሎማሲ ውጤትን ያበላሸውና ለትልቅ ኪሳራ ያበቃንን የኤርትራን ፌዴሬሽንን አፈረሱ፡፡ ውጤቱም ሁላችንም እንደምናውቀው፤ የኤርትራ ነፃ አውጪ ግንባር መፈጠር ሆነ፡፡ ትንሽ ቆይቶ ደግሞ ኦሮሞዎች የሜጫና ቱላማ ልማት ማህበር በመፍጠራቸው፤ ጠገቡ ተብሎ መሪዎቹ እነ መቶ አለቃ ማሞ መዘምር ተሰቀሉ፡- ኃይለማርያም ገመዳ እስር ቤት ውስጥ በተፈፀመበት ድብዳባ ሞተ፡፡ ጀኔራል ታደሰ ብሩ ሞት ተፈርዶባቸው በአማላጅ ወደ ሐረርጌ በግዞት ተላኩ፡፡ እኔ እስከ ማውቀው ድረስ ሁሉም በኢትዮጵያ አንድነት ላይ ጥያቄ አልነበራቸውም፡፡ ውጤቱ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ)ን መፍጠር ሆነ፡፡ በነገራችን ላይ በነኤሌሞ ቅልጡ በኦነግ ስም የመጀመሪያዋ ጥይት የተተኮሰችው ጀኔራል ታደሰ ብሩ የታሰሩበት ሥፍራ ሐራርጌ ዉስጥ ነበር፡፡ü በዚሁ ጊዜ ሰፋፊ ማህበራዊ ፍትህን የሚጠይቁ ተከታታይ ጥያቄችም መቅረብ ጀመሩ፡፡ እአአ በ1965 የንጉሱ ፍዉደለዊ ሥርአት የተመሠረተበት ላይ በመሬት ላራሹ ሰልፍ ድንገተኛ የፖለቲካ ቦንብ ፈነዳ፡፡ ከአራት ዓመት በኋላ ደግሞ እስከዛሬ ኢትዮጵያን እያመሰ ያለው፤ በነዋለልኝ መኮንን የብሔረሰቦች ጥያቄ ታወጀ፡፡ ይህችኛውን ንጉሱና ሥርአቱ በቀላሉ የተመለከቱዋት አይመስልም፡፡ ንጉሱ የቀ.ኃ.ሥ ዩኒቬርሲቲ፤ የአሁኑ አዲስ አበባ ዩኒቬርሲቲ ተማሪዎች ማህበር ፕሬዝዳንት የነበረውን፤ ጥላሁን ግዛዉንን በማሰገደል “ልጆቼ ” ከሚሏቸው ተማሪዎች ጋር ደም መቃባት ዉስጥ ገቡ፡፡ በዚህም የታሪክ ጎማው ወደፊት እንዳይሽከረከር ጣሩ፡፡ü አሰዘኙ ጉዳይ መካሪዎቻቸውም ሆኑ እሳቸው አስተዳደራቸው ለሃኛዉ ክፍለ ዘመን የማይመጥን መሆኑን፤ በጣም እወዳታለሁ የሚሉዋትም ኢትዮጵያ በታሪክ ፍራሽ ላይ ተኝታ የምትሸሞነሞን ሀገር መሆንዋን አልተረዱም፡፡ የኤርትራ ግንባሮች ጥይትም ከረጅም ዘመን እንቅልፋቸው አላነቁአቸውም፡፡ ü የባሌና የጎጃም ሕዝብ አመፅም አልቃሳቀሰቸውም፡፡ ለዓመታት የቆየው የተማሪዎች ንቅናቄ ጩሀትም አላነቃቸውም፡፡ ከኢትዮጵያ ተማሪዎች ንቅናቄ በቀጥታ የወጡ የመኢሶንና የኢህአፓ የሶሻሊስት አብዮት ደወልም አላነቃቸውም፡፡ በመጨረሻም በመቶ ሺዎች የሚቆጠረው የወሎ ሕዝብ እልቂት እንኳን ከእንቅልፋቸዉ አላባነናቸውም፡፡ በነገራችን ላይ፤ ብልጡ ደርግ በጠዋቱ ሊያወርዳቸው ፣ ማታ ያሳየው የወሎ ሕዝብ እልቂት፤ በአንድ በኩል የንጉሱ ውሻ በጮማ ሥጋ ሲጫወት፤ በሌላ በኩል ደግሞ በረሃብ በተረፈረፈ ሕዝብ ውስጥ ሕፃን ልጅ የሞታች እናቷን ጡት ሲትጠባ የሚያሳየዉን የጆናታን ድንብልብይ ፊልም ነበር፡፡ ያንን ፊልም ደርግ በቅድሚያ ንጉሱና የኢትዮጵያ ሕዝብን እንዲያዩ ስለጋበዘ ቴሌቪዥን ያልነበረን የዩኒቬርሲቲ ተማሪዎች በስድስት ኪሎና አራት ኪሎ አከባቢዎች ያሉትን ቡና ቤቶችን አጣብበን ስንመለከት ነበር፡፡ የንጉሱ ደጋፊዎች እንከዋ፤ ጃኖሆይ እንዲህ ጨካኝ ነበሩ እንዴ? የሚሉትን ይዘን ወደ ዶርማችን እንደገባን ትዝ ይለኛል፡፡ ምናልባት ከእንቅልፋቸው የነቁት በማግስቱ የደርግ አባላቱ በኩምቢ ቮልስዋገን ከቤተመንግስታቸው ወደ አራተኛ ክፍለ ጦር ሲወስዷቸው በሰሩባቸው ድራማ ይመስለኛል፡፡ ብልጣብልጦቹ ደርጎች የተጠቀሙት ቮልስ መጀመሪያ መስኮቷ ዝግ ነበር ይባላል ፡፡ü ንጉሱ ከውጭ ብዙ ሰው ሲጮህ ተመልክተው “እናንተ ልጆች” የምወደን ሕዝባችን ንጉሴን የት እየወሰዳችሁ ነው እያለ ነዉ ሲሉ፤ ብልጦቹ ደርጎችም መስኮቱን ከፍተው የሕዝቡን ድምፅ ሲያሰሟቸው ጩኼቱ “ተፈሪ ሌባ፤ ተፈሪ ሌባ” የሚለውን ሰምተው “አይ ኢትዮጵያ ይኼን ያክል በድዬሻለሁ እንዴ?” አሉ ይባላል፡፡ ü በዚህ ሽኝታቸው ድሮ ቤተክርስቲያን ሲሄዱ ዳቦ የሚጥሉላት ለማኝ ዳቦዋን ሲትጠብቅ ንጉሱ ወረዱ፤ ንጉሱ ወረዱ ሲባል ሰምታ፣ ለዚህ ያበቃኼኝ አንተ ነህ ብላ በቮልሷ አቅጣጫ የወረወረችው ዳቦ ብቻ ነበር ይባላል፡፡ የንጉሱ ሬሳም ከ17 ዓመታት በኋላ ከመንግስቱ ኃይለማርያም ሽንት ቤት ሥር ተቆፍሮ እንደተገኘ ይታወቃል፡፡ እዚህ ላይ ልብ አድርገን ማለፍ ያለብን የፖለቲካ ቁም ነገር ለ60 ዓመታት ገደማ (የአምስት ዓመቱ የጣሊያን ወረራ እንዳለ ሆኖ) በፈላጭ ቆራጭነት ኢትዮጵያን ሲገዙ የሀገረ መንግስታቸው ግንባታ ፕሮጀክት በአጉል ምክርም ይሁን በራሳቸው ገታራ አቋም ከሽፎ ሽኝታቸው በለማኟ ዳቦ፣ ቀብራቸው ደግሞ በአሳደጉአቸው ወታደሮች ሽንት ቤት ሥር መሆኑ ነው፡፡
3. አብዮቱ እና የደርግ የሀገረ-መንግስት ግንባታ ሙከራ፡-ü አዲስቷን ኢትዮጵያን ለመፍጠር ሕዝባዊ አብዮቱ ልዩ ዕድል ፈጥሮ ነበር፡፡ አብዮቱ ከተለያዩ የኢትዮጵያ ማህበረሰቦች የመጡ የአዲሱ ትዉልድ ምሁራን ድጋፍና ተሳትፎ ነበረው፡፡ እንደ አብዮቱ መሪ ወደፊት የመጣውን መንግስቱ ኃይለማርያምም ቪቫ መንግስቱ፣ ቪቫ መንግስቱ ብለን ተቀብለን ነበር፡፡ü የኢትዮጵያ አብዮትን አብዮት ያደረገው የጭሰኝነት ሥርአትን ያስወገደውና የደርግ እርምጃ (ውለታው የኢትዮጵያ ተማሪዎች ንቅናቄ ቢሆንም) እስከዛሬ በኢትዮጵያ የሕዝቦች የትግል ታሪክ ውስጥ ልዩ ሥፍራ አለው ብዬ ባምንም ነገሮችን በቶሎ የሚያዩ ወጣቶች “ተፈሪ ማረኝ፣ የደርጉ ነገር አላማረኝ ” ማለት የጀመሩት ብዙዉም ሳይቆዩ ነበር፡፡ በአጭሩ ለማስቀመጥ የደርግ ሥልጣን ፍቅር፣ የመኢሶንና የኢህአፓ አሳዛኝ ክፍፍል፤ የኤርትራ ግንባሮችና የሕወሓት የተናጠል የፖለቲካ ፕሮጀክቶች በአብዮቱ መፈንዳት የተፈጠረውን ልዩ ታሪካዊ ዕድል አምክኖታል፡፡ደርግ መሃይምነትና የሥልጣን ፍቅር ስለተደባለቀበት፤ የሶሻሊስት አብዮቱን እንደሰው ማሰርና መግደል ወሰደው፡፡ በዚህ ሶቭዬት ህብረት ድረስ ሄዶ የሌኒን ሐውልት አይተው የመጡት በለሥልጣኖቹ ስለሶሻሊዝም የተማርነው ከበሰበሰ ከቡርዧ ቤተ መፃሕፍት ሳይሆን፤ ከምንጩ ከሌኒን ሀገር ነው እያሉ ተዘባበቱ፡፡ ካደሬዎቻቸው ድንቅ የሶሻሊስት ዕውቀታቸውን ከፍተኛነት ለማሰየት በሚመስል መንገድ የእስታሊን ቀይ በትር ሥራ ላይ ይዋል አሉ፡፡ ደርግ የሱማሌ ወረራን፣ የኤርትራ ግንባሮችና የህወሓት እንቅስቃሴዎች በኢትዮጵያ አንድነት እንዲነግድ ልዩ ሁኔታ ስለፈጠሩለት “ አብዮታዊት እናት ሀገር ወይም ሞት ” አለ፡፡ ከኤርትራ ግንባሮች እስከ ኢህአፓ እና መኢሶን (ኢጭአት/ኦነግን ጨምሮ ሌሎች ድርጅቶች እዚህ መሃል ናቸው) የኢትዮጵያ ሕዝቦች የአንድነትና የአብዮት ጠላቶች ሆነው ልዩ ልዩ ስሞች ተለጣፈበቸው፡፡ በአጭሩ የኢህአፓና መኢሶን መከፋፈልም ደርግን ብቻኛ የሀገር አንድነትና የአብዮት ተወካይ አደረገው፡፡ሌሎች ዝርዝሮችን ትቼ ለኢትዮጵያ አንድነትና አብዮት ግንባታ ወሳኝ የሆኑ ዕርምጃዎችን ላንሳ፡፡ የደርግ የመጀመሪያው ሊቀ መንበር፣ አማን አንዶም የሚባሉ ኤርትራዊ ጀኔራል ነበሩ፡፡ የደርግ ሊቀ መንበር ተብሎ ከደርግ ውጭ የተመረጠትም ለኢትዮጵያ አንድነት ብሎ እስከ ሞቃዲሾ ድረስ ሄዶ ካልተዋጋሁ ብሎ ንጉሱን ያስቸገሩ መኮንን ስለነበሩ ነዉ፡፡o በወታደሮቹ ዘንድም ተወዳጅ ስለነበረ በራሳቸው በደርግ አባሎቹ ጥያቄ መጀመሪያ መከላከያ ሚኒስቴር፤ ከዚያም ከደርግ ውጭ የደርግ ሊቀ መንበር የሆነው የተመረጡትና በአደባባይ እስከሚታወቀውም በኢትዮጵያ አንደነት ላይም (መቼም በኢትዮጵያ አንድነት ላይ ልዩ ፍቅር አለን የሚሉ ብዙ ቢኖሩም፤ ፍቅራቸውን የሚለካልን መሳሪያ በሜዲካል ሳይንስ እስካሁን አልተፈጠረልንም) ምንም ዓይነት ጥያቄ ያልነበራቸውና የኤርትራን ችግር በሠላም ለመፍታት አስመራ ድረስ ሄዶ ሕዝቡን ያወያዩ ነበሩ፡፡ ለኢትዮጵያ ልዩ ፍቅር አለኝ የሚሉ እነሻለቃ መንግስቱ ኃይለማርያም ግን ጠረጠሩዋቸዉ፤በታንክ እቤታቸው ውስጥ ገደሉት፡፡ በእኔ ግምት ውጤቱ የኤርትራና የኢትዮጵያን አንድነት መግደል ነበር፡፡ በዚህም ኤርትራ የደም ምድር ሆነች፡፡ ዛሬ እንዲህ ልንሆን የፈሰሰው የሰው ደም ዋጋም ሆነ ለጠፋው ሀብትና ንብረት ሂሳብ ለፈረደበት ታሪክ መተው ይመረጣል፡፡ü የብሔራዊ አንድነት መንግስትን ሊታመጡብኝ ብሎ መንግስቱ ኃይለማርያም ሁለተኛውን የደርግ ሊቀ መንበር የነበሩትን ጀኔራል ተፈሪ በንቲን ከደጋፊዎቻቸው የደርግ አባላት ጋር ረሸናቸው፡፡ ኮሎኔል አጥናፉ አባተንም ቅይጥ ኤኮኖሚ ሊታመጣብን ነው ብሎ መንግሥቱ ኃይለመሪም በፀረ-አብዮታዊነት ረሸነዉ፡፡ በነገራችን ላይ የመጨረሻ ጭንቅ ሲመጣ መንግስቱ ኃይለማርያም የአጥናፉን ቅይጥ ኤኮኖሚ ላይ ለመንጠላጠል ሞክሮ ነበር፡፡4. በዛሬው የኦሮሞ ፖለቲካ ውስጥ ልዩ ሥፍራ ያላቸው ጀኔራል ታደሰ ብሩ ለሁለተኛ ጊዜ ሞት ተፈርዶባቸው ተረሸኑ፡፡ እኔ መከታተል እስከቻልኩ ድረስ ታደሰ ብሩ በኢትዮጵያ አንድነት ላይ ፍጹም ጥያቄ ያልነበራቸው፤ ለኢትዮጵያ ብሎ ከሰላሌ ጫካ እሰካ ሞቃዲሾ ድረስ ተወስደው የታሰሩ እንግሊዞች ኢትዮጵያ ነፃ እናወጣለን ብለው ሲመጡ ከነሱ ጋር እየተወጉ የመጡ አርበኛ ነበሩ፡፡ ከተራ ወታደርነት እስከ ጀኔራል ማዕረግ ድረስ ሀገራቸውን ያገለገሉም ነበሩ፡፡ እግር ጥሏቸው አብዮቱ ውስጥ የገቡት መንግስቱ ኃይለማርያም ያላርህራሄ ገደሏዋቸዉ፡፤ በነገራችን ላይ ከጀኔራል ታደሰ ብሩ ጋር በፀረ አንድነት ክስ የተገደለ፤ ብዙ ሰው የማያስታውሰው፤ መለስ ተክሌ የሚባል በቀ.ኃ.ሥ ዩኒቬርሲቲ ከተማሪ መሪዎች አንዱ የሆነ የትግራይ ተወላጅ ነበር (በግዜዉ ከነበረዉ አቋም ተነስቼ፤ ይህ ሰው ቢቆይ ኖሮ የትኛው ድርጅት ውስጥ ሊገባ እንደሚችል ዶክተር አረጋዊን ደግሜ መጠየቄን አስታውሳለሁ)፡፡ ይህ ሰዉ፤ ሌላ ተከታይ ቢያጣ ለሩብ ምዕተ ዓመት አከባቢ የምኒልክ ቤተመንግስትን ተቆጣጥሮ በፈላጭ ቆራጭነት ሀገሪቷን የገዛው ለገሠ ዜናዊ ስሙን አንስቶ ትግራይ በረሃ ገብቷል፡፡ ይህም ደርግ በኢትዮጵያ አንድነት ስም ያመጣብን የታሪክ ዕዳ ነው፡፡ በኢትዮጵያ አንድነት ላይ ምንም ዓይነት ጥያቄ እንዳልነበራቸው በተሻለ የማውቃቸውን የመኢሶን መሪዎችን ላንሳ፡፡ ለሥልጣን ተብሎ በደርግና ብዙ የፖለቲካ ተቀናቃኞቹ ዘንድ እንደ ኦሮሞ ድርጅት፤ በኦሮሞ ደግሞ እንደነፍጠኛ ድርጅት የሚታየው መኢሶን በዘመኑ በየትኛውም ሚዛን የተሻለ ትምህርት የነበራቸው መሪዎች ነበሩት በስብጥራቸውም ኤርትራዊ የዘር ግንድ አላቸው ከሚባሉት ኅሩይ ተድላ እና አበራ የማነአብ እስከ ሲዳማው እሼቱ አራርሶ የነበሩበት ነው ፡፡ ሹኩሪ የሚባል አዲስ አበባ ዩኒቬርሲቲ አብረን የነበርነው ልጅ በስተቀር ሰፊ ተሳትፎ እንደልነበራቸዉ የማዉቀዉ የሱማሌ ምሁራንን ብቻ ነበር ፡፡ የመጀመሪያዉ የመኢሶን ሊቀ መንበር የሰሜን ሸዋ አማራ ከሚባለው የተወለዱ፤ ዶ/ር ወርቁ ፈረደ፤ ሁለተኛው ኃይሌ ፊዳ፤ ሦስተኛው የወሎ አማራ ከሚባለው የመጡ፤ ዶ/ር ከበደ መንገሻ ነበሩ፡፡ ሕብረ ብሔር ነን፣ ለሀገረ- መንግስት ግንባታው የተሻለ ግንዛቤም እዉቀትም አለን ለሚሉ የመኢሶን ምሁራንም ደርጎች ርህራሄ አላደረጉም፡፡ü በተለይ የመጀመሪያው የኦሮሞ የምሁር ትዉልድ የሚባሉት ኃይሌ ፊዳን ጨምሮ አብዱላህ ዩሱፍ፣ ዶ/ር ከድር መሀመድ፣ ዶ/ር ተረፈ ወልዴፃዲቅ፤ ደ/ር መኮንን ጆቴ የመሳሰሉት ሕበረ ብሔር በሚበለው መኢሶን ውስጥ አልቀዋል፡፡ በኔ እምነት፡ ብዙዎች ሊቀየሙኝ ቢችሉም፤ እንደስማቸው በኢትዮጵያ ምድር ሕብረ ብሔር የነበሩ ድርጅቶች መኢሶንና ኢህአፓ ብቻ ነበሩ፡፡ አላስፈላጊ ክርክር ዉስጥ ሳልገባ፤ እኔ እስከ ማምነው ድረስ ኢሠፓ የወታደሮች ፓርቲ ነበር፡፡ የኢህአዴግን ምንነት ለብልፅግና አበለት እተዋለሁ፡፡ የብልፅግናን ምንነት ደግሞ የታሪክ ፈተናዉን ሲያልፍ ብንነጋገርበት የተሻለ ይመስለኛል፡፡ ደርግ ሕበረ ብሔር ድርጅቶችን በቀላሉ አንድ በአንድ ቀርጥፎ በላቸው፡፡ ኢህአፓን ቁርስ አደረገ፤ መኢሶንን ምሳ አደረገ:: ብሔር ሆኖ ለመውጣት ገና ዳዴ የሚሉትን ወዝሊግንና ማሌሪድን እራት አደረጋቸው፡፡ ከደርግ ዱላ የተረፉት በደርግ አስተዋጽኦ ጭምር በተሸለ ሁኔታ ኃይል ሆነዉ የወጡት የብሔር ንቅናቄዎች ናቸው፡፡ ü ኢጭአት ወደ ኦነግ ተጠቃልሎ ገብቶ ዛሬ የምናውቀው ኦነግን ፈጠረ፡፡ የሱማሌ ድርጅቶች ኦብነግ ዓይነትን ፈጠሩ፡፡ የሲዳማ አርነት ንቅናቄ ቢያንስ ዋናው ክንፍ ዛሬ ሲአን የሚለው ሆነ፡፡ አፋሮችም የአፋር ግራ ክንፍ አርዱፍ እያሉ በሕይወት ያሉ ድርጅቶች አሏቸው፡፡ በጣም የተሳካላቸው የብሔር ንቅናቄዎች በኢትዮጵያና ኤርትራ ላይ ደርግን ለሁለት ቀብረው መንግስታት ሆኑ፡፡ የደረግ ዘመንን ስናጠቃልል መረሳት የሌለባቸው ሦስት ዋና ዋና ጉዳዮች፣ ለሥልጣን ብሎ ደረግ ባካሄዳቸው ጦርነቶች፡-ü የሀገረ-መንግስት ግንባታውን የበለጠ አወሳስቦ መሄዱን፣ ሻለቃ ዳዊት ወልዴጊዮርግስ በፃፉት መጽሐፍ በትክክል እንዳስቀመጡት ደርግ ትቶት የሄደው በደም እምባ የታጠበች ሀገር መሆንዋን፣ü በሀገር አንድነት ስም ባካሄደው ትርጉም የለሽ ጦርነት የባከነው የሀገር ሀብት ብቻ ሳይሆን በዓለም ትልቋ ወደብ አልባ አገር ኢትዮጵያን ትቶ መሄዱን ነዉ፡፡ደርግ ለ17 ዓመታት የተጨወተዉ የአጥፍቶ መጥፋት ፖለቲካን፤ እንደ ኑዛዜም፤ እንደቁጭትም የደርግ ከፍተኛ ባለሥልጣን የነበሩት ኮሎኔል ፍስሃ ደስታ (ኮ/ል መንግስቱ ኃይለማርምም ሆነ ሻምበል ፍቅረ ሥላሴ ወግደረስ እዳፋቸውን ከታጠቡበት በጣም ይሻላል) በፃፉት መጽሐፍ ልዝጋ፡፡ የኢህአፓ ወጣቶችን የትግል ስሜት፤ የመኢሶን መሪዎች ዕውቀትና የእኛን የወታደሮቹን የአገር ወዳድነት ብንጠቀምበት ኖሮ ሀገራችን እንዲህ አትሆንም ማለታቸውን እስር ቤት ሆኜ ማንበቤ ትዝ ይለኛል፡፡ ምክራቸው ለጠቅላይ ሚኒስትር አቢይም የሚሆን ይመስለኛል፡፡ በነገራችን ላይ፤ በታሪክ አጋጣሚ ወደ አስር ወሮች ገደማ በኢህአዴግ እስር ቤት የተኛሁበት አልጋ ኮ/ል ፍስሃ ደስታ ይተኙበት እንደነበረ ሰምቻለሁ፡፡
4. የኢህአዴግ ዘመን የሀገረ መንግስት ግንባታ፡- ለአራተኛ ጊዜ የሀገራችን ፖለቲካን ማሰልጠንና የተሻለ የሀገረ መንግስት ግንባታ ዕድል ያመለጠን የኢህአዴጉ ዘመን ነው (ይህ የመለስ እና የኃይለማርያም ዘመንን ይጨምራል)፡፡ü የኢህአዴግ ዘመን፤ ሌላው ቢቀር የብሔረሰቦች ጥያቄን ለሁሉም ሕዝቦች ተቀባይነት ባለው መንገድ ይመልሰል ብሎ (እኔን ጨምሮ) የጠበቁ ብዙ ናቸው፡፡ ይህም ለሀገረ መንግስት ግንባታ የተሻለ ዕድል ይፈጠራል ተብሎም ተገምቶ ነበር፡፡ ገና የሽግግር መንግስቱ ሲመሠረት የኢህአዴግ ባለሥልጣናት እንደግል ሠርጋቸው የፈለጉትን ጠርተው፤ ያልፈለጉትን በመተው የሰሩት የፖለቲካ ቲያትር ጫካ ሆነው ስደግፋቸው ከነበሩት የኢህአዴግ መሪዎች ተለየሁ፡፡ü እኔም ብቻ ሳልሆን ብዙ የአዲስ አበባ ዩኒቬርሲቲ መምህራን ጓደኞቼ በዚህ ጊዜ የተለዩዋቸዉ ይመስለኛል፡፡ü ኢሀአዴግ መጀመሪያ በጦርኛነት፤ ቀጥሎ ደግሞ በዘመኑ ቋንቋ የሽብርተኝነት ታርጋ እየለጠፈ ለ27 ዓመታት ሕዝብና ሀገርን አመሰ፡፡ ዝርዝር ነገሮች ውስጥ ሳልገባ፤ በኦሮሚያ እና በሱማሌ ክልሎች፤ በሲዳማ፣ በሀዲያ፤ በወላይታ፣ በጋምቤላ፣ በአፋር፣ ቁጥራቸውን የኢህአዴግ ባለሥልጣናት እንኳ የማያውቁት ሕይወት ጠፋ፡፡ü የአፍሪካ መዲና የምትባለው አዲስ አበባ/ፊንፊኔም ሆነች የኢህአፓን ጠበል በቀመሱ ብአዴኖች የሚመራው የአማራ ክልልም ውሎ አድሮ ከኢህአዴግ ዱላ አልተረፉም፡፡ ü በአብዮታዊ ዴሞክራሲ ርዕዮተ ዓለም (ነገርየው መሬት ላይ ሲፈተሸ፤ የአብዮታዊነትም የዴሞክራሲያዊነትም ባህርይ አልነበረውም) የተተበተበው የሞግዚት አስተዳደር ዕውነተኛ የፌዴራል ሥርአት ሊሆን አልቻለም፡፡ü የሕዝቦችን እራስን በራስ ማስተዳደር ጋር ምንም ግንኙነት ያልነበረው፤ ጆርጅ ኦርዌል፤ የእንስሳት እርሻ በሚለዉ መጽሐፉ ላይ፤ ሁሉም እንስሶች እኩል ናቸው፤ አንዳንድ እንስሶች የበለጠ እኩል ናቸው “All animals are equal, some are more equal than others” ከሚለው ያለፈ የፖለቲካ ፋይዳ አልነበረውም፡፡ ü ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ተብዬዎቹም ከ97ቱ በስተቀር ዴሞክራሲያዊ ሥርአት መፍጠር ይቅርና ቅርጫ እንኳ ልሆኑ አልቻሉም፡፡ ዉጤቱም ዴሞክራሲያዊ የሀገረ-መንግስት ግንባታ ዕድል መጨናገፉ ብቻም ሳይሆን ለ27 ዓመታት ውድ የሕይወት ዋጋ ጭምር ሲያስከፍለን ኖሯል ፡፡ ü በዚህም ምክንያት የታሪክ ጣጣችንን አስተካክለን በእኩልነት ላይ የተመሠረተ ዴሞክራሲያዊ ፌዴራሊዝም የመፍጠር ተስፋችን ሕልም ሆኖ ቀርቷል፡፡
5. በማምለጥ ላይ ያለ አዲስ የሀገረ-መንግስት ግንባታ ሙከራ፡- አሁን እየገጠመን ያለውን የታሪክ ፈተናን ለመለፍ፤ ጨክነን በቁርጠኝኘት ብሔራዊ መግባባት ውስጥ መግባት ወይም ኢትዮጵያን እንደ ሀገረ-መንግስት የምታበቃበት የሚጨምር ቀውስ ውስጥ መግባት ይመስለኛል፡፡ እዚህ ላይ የሌሎች ሀገሮችን ፖለቲካ በድህረ ቅኝ ግዛት ዘመን ብቻ እንኳን በመቀኛት ብጀምር፤ ችግሮቻቸውን ለመፍታት በቁርጠኝነት የሰሩት ተሳክቶላቸዋል፡፡ ያንን ያልቻሉት ወይ ፈርሰዋል ወይም አሁንም በቀውስ ውስጥ እየደከሩ ነዉ፡፡ ቅኝታችንን በላቲን አሜሪካ ብንጀምር፤ቃዉስ ገጥሙዋቸዉ አነ አርጀንቲና፣ ችሌ፣ ፔሩ፣ ኒካራጉዋ፣ ኮሎምቢያ የመሰሰሉ ሀገሮች፣ በተለያየ ደረጃ ፖለቲካቸውን ያስተካከሉ ሀገሮች ናቸው፡፡ ከ60 ዓመታት በላይ ለልዕለ ኃያሏ አሜሪካ ሳትበገር በአሜሪካ አፍንጫ ሥር የኖረችው አስደናቂዋ ሶሻሊስት ኩባና በአሜሪካ ጣልቃ ገብነት ምክንያት አሁን በሁለት ፕሬዝዳንቶች የምትገዛዋ ሶሻሊስት ቬኔዙዌላም በዚሁ ክፍለ ዓለም ይገኛሉ፡፡ በአውሮፓ ፖርቹጋል፣ ስፓኝ፣ ግሪክ፣ ፖለቲካቸዉን ማስተካከል ችለዋል፡፡ ዩጎዚላቪያ ውድ ዋጋ ቢትከፍልም ከመፍረሰ አልደነችም፡፡ ሶቭዬት ህበረትና (ግማሽ አውሮፓ ነች) ቼኮዚላቫኪያ በሰላማዊ መንገድ ፈርሷል፡፡ በኤሽያ፤ ኔፓል የፓለቲካ ችግረዋን በብሕራዊ መግባባት ስትፈታ፤ ፓክስታን፤ ቬየትናም፤ ካምቦዲያና ላኦስ ደግሞ ችግሮቻቸውን በጦርነት ፈተዋል፡፤ አፍጋንስታን፣ ኢራቅ፣ ሶሪያና የመን አሁንም እየቀወሱ ነው፡፡ ወደ አፍሪካችን ስንመጣ፡ ደቡብ አፍሪካና ጋና ከመሳሰሉት በስተቀር አብዘኛዎቹ በይስሙላ ምርጫ ላይ የተመሠረቱ አምባገነን መንግስታት ሲሆኑ፤ የአፍሪካ ሕብረትም የዲክታተሮች ማህበር (trade union of dictators) ከመሆን አላለፈም (በኢህአዴግ ጊዜ የተከሰስኩበት አንዱ ወንጀሌ የአፍሪካ መሪዎችን ተሰደብክ የሚል ነበር)፡፡ ሱማሊያና ሊቢያ፤ ፈረንጆች የወደቁ መንግታስት (failed states) የሚሉት ሲሆኑ፤ ሩዋንዳ ጊዜውን ጠብቆ የሚፈነዳ ሌላ ቦንብ የምትጠብቅ ይመስለኛል፡፡ በዚህ የአፍሪካ ፖለቲካ ምስቅልቅል ጉዞ ውስጥ አንዱ የሚገርመኝ ላለፉት 60 ዓመታት ፖለቲካቸውን ማስተካከል አቅቷቸው በቀውስ ሲናጡ የኖሩ ሁለት ሀገሮች፤ በተፈጥሮ ፀጋ እጅግ ሀብታሟ የኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፑቢሊክና የሦስት ሺህ ዓመታት ዕድሜ አለኝ የምትለዋ ድሃዋ ኢትዮጵያ መሆናቸው ነው፡፡ ከንጉሱ ዘመን ጀምሮ ይህንኑ የሀገራችንን የፖለቲካ እንቆቅልሾችን የተከታተለ፣ ያጠና፣ ያስተማረና ብዙ ጽሑፎችን የፃፈበት ጆን ማርካከስ የሚባል ፈረንጅ፤ የታሪክና ፖለቲካ ሳይንስ ፕሮፌሴር “Ethiopia: The Last Two Frontiers” (የኢትዮጵያ የመጨረሻዎቹ ሁለት ድንበሮች) ብሎ ፅፎአል፡፡ ምሳ ጋብዞኝ መፅሐፉን ለዶ/ር አቢይ ስጥልኝ ብሎኝ፤ ዶ/ር አቢይ ያንብበው አያንብበው ባላውቅም፤ እሳቸውን ማግኘት ለሚችል ለኦፒድኦ ባለሥልጣን ልኬላቸዋለሁ እንደነበርም አሰታዉሰለሁ፡፡ መፅሐፉ በአጭሩ የኢትዮጵያ መሪዎች የሀገረ-መንግስት ግንባታ፤ የንጉሶቹ ሞዴል (the Imperial model) የደርግ የሶሻሊስት ሞዴልና የኢህአዴጉ ፌዴራሊስት ሞዴል በሙሉ ከሽፈዋል ይላል፡፡ የከሸፉበትም ዋናዉ ምክንያት፤ የባለጊዜ ገዥዎችን ሥልጣን ለማሳካት የተገፋበት መንገድ የኢትዮጵያ ሕዝቦችን እኩልነት ያላጎናፀፈና የልማት ጥማታቸውንም ያላረካ በመሆኑ ነው ይላል፡፡ ይህ የፈረንጅ ምሁር እንዳለው፤ ፖለቲካችንን ማሰልጠን ባለመቻላችን ሚሊየኖች ሕይወታቸውን አጥተዋል፤ ሚሊዮኖች ከቄዬያቸው ተፈናቅለዋል፤ ሚሊዮኖችም ተሰደዋል፡፡እኔም ከላይ ባነሳሁት ከዚሁ ምሑር ዕይታ ተነስቼ ሀገራችን ስለገባችበት የፖለቲካ ቅርቃርና በብሔራዊ መግባባት አንፃር ከቅርቃሩ ለማውጣት በሌኒን ቋንቋ ምን መደረግ አለበት (What is to Be Done?) የሚለውን መሠረታዊ ጥያቄ የሀገራችን ፖለቲካ እስከገባኝ ድረስ ልመልስ፡፡
1. መሠረታዊ ችግራችን በታሪክ አጋጣሚ ሥልጣን ላይ የወጡ መሪዎቻችን ሀገርን የመምራት ሕልማቸው፤ ሥልጣንን ጨምዲዶ ከመቆየት ሕልማቸው ጋር ሁሌ ስለሚጋጭባቸው ነው፡፡ ለሕዝብ አለን ከሚሉት ፍቅር የሥልጣን ፍቅራቸው ስለሚበልጥባቸው ነው፡፡ o ለዚህ ነው ንጉስ ኃይለ ሥላሴ የምወደንና (ሕዝቡ ምን ያከል እንደሚወደቸዉ እንዴት እነዳወቁ ባናዉቅም) የምንወደው ሕዝባችን ሲሉ ኖረው ለ60 ዓመታት ገደማ የገዟትን ኢትዮጵያ ለ20ኛዉ ክፍለ ዘመን ሳያበቁ፤ ከዓለም ሀገሮች ጭራ ደረጃ ትተዋት የሄዱት፡፡ የሕዝብ ፍቅራቸውንም ደረጃ በረሃብ በመቶ ሺህዎች ያለቀው የወሎ ሕዝብ ይመሰክራል፡፡ ይህን የመሳሰሉ የመሪዎቻችን ባዶ የሕዝብና የሀገር ፍቅር፤ የንጉሱ ሕይወቴና የኢትዮጵያ እርምጃ፣ የመንግስቱ ኃይለማርያም አብዮታዊት እናት ሀገር ወይም ሞት የመለስ ዘናዊ በቀን ሦስት ጊዜ የሚመገቡ ዜጎችን እፈጠራለሁ ወ.ዘ.ተ መሸፈን አይችልም፡፡o ለዚህ አሁን ያሉ መሪዎቻችንም ሆኑ ተስፈኛ መሪዎች ይህንን የታሪክ እውነታ በውል እንዲገነዘቡት እፈልጋለሁ፡፡
2. የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎችና የተቀሩት ሊሂቃን፣ በተለያየ ደረጃ የሚጋጩ ሕልሞቻቸውን ይዘው መጓዛቸው ነው፡፡o ከመኢሶንና ኢህአፓ ዘመን እስከዛሬ ያሉ የፖለቲካ ድርጅቶቻችንና መሪዎቻቸው ይህንን እውነታ በውል መገንዘብ ይኖርባቸዋል፡፡ የሕልሟን ጉዳይ በፈንጆቹ አባባል ከዜሮ ድምር ፖለቲካ (Zero-Sum game Politics) የመውጣቱን ጉዳይና የፖለቲካ ፍላጎቶቻቸዉን በገደብ የማድረጉን ነገር በጥብቅ እንዲያስቡበት እመክራለሁ፡፡ ዋና ጉዳያችን ሥልጣን ሆኖ ከፊንፊኔ እስከ መቀሌ ባንዳ፤ ባንዳ እየተባባሉ መካሰሱ ሕዝባችንን ከማደናገር በላይ ብዙ የፖለቲካ ትርፍ የለውም፡፡o ዛሬ በአሜሪካና በአውሮፓ በሚደረጉ ሰልፎች ላይ በአንድ እጅ እስክንድር ነጋ ይፈታ፣ በሌላ እጅ ጃዋር ሽብርተኛ ነው የሚሉት መፈክር ዓይነቶቹ ለሀገረ-መንግስት ግንባችንም ሆነ ለብሔራዊ መግባባት ሥራችን ብዙ የሚጠቅሙ አይመስሉኝም፡፡ በኔ በኩል እንዲህ ዓይነቱ ጉዳይ ስላስቸገረኝ ነበር፤ በ2008 በፃፍኩት መፅሐፍ ላይ ለቡዳ ፖለቲካችን መላ እንፈልግ ብቻ ሳይሆን የሚጋጩ ሕልሞች ሊታረቁ ወይስ ኢትዮጵያን ሊያፈርሱ በሚል ግልፅ ጥያቄ የደመደምኩኝ፡፡ o ለኔ መፍትኼው ለአዲስቷ ኢትዮጵያ ፈጠራ የሚሆን አዲስ ማህበራዊ ውል (New Social Contract) ከመፈራረም ውጭ የተሻለ የማጂክ ፎርሙላ ያለን አይመስለኝም፡፡ o ይህንን እውነታ የምኒልክ ቤተመንግሰት ያሉ የብልፅግና ወንድሞቻችንም ሆኑ ከአዲስ አበባ/ፍንፍኔም እስከ አውሮፓና አሜሪካ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ግፋ በለው የሚሉ ሁሉ እንዲረዱልኝ አደራ እላለሁ፡፡o በቅርብ ጊዜ በተፈጠረው ቀውስ በሁሉም በኩል ላለቁትም የተሻለ የሐዘን መግለጫ የሚሆነውና ዕንባቸውን የሚያብሰው የችግሮቻችን ምንጭ አዉቀን ዘለቂ መፍትኼ ስንፈልግ ይመስለኛል፡፡3. እላይ ካነሳሁኝ ሁለት ነጥቦች ጋር ተያይዞ፤ ሺህ ጊዜ ነፃና ፍትሐዊ ምርጫ እየተባለ በሕዝብ ላይ የሚሰራዉ የፖለቲካ ትያትር መቆም አለበት፡፡o የንጉሱ ዘመን የምርጫ ትያትሮች፣ የደርግ ዘመን የምርጫ ትያትሮች፣ የኢህአዴግ ዘመን የምርጫ ትያትሮች በግልፅ ቋንቋ ለማስቀመጥ፤ ሲያንሱ በዴሞክራሲ ስም የተቀለዱ ቀልዶች፤ ሲበዙ ደግሞ በኢትዮጵያ ሕዝቦች ላይ የተሰሩና ታሪክ ይቅር የማይላቸው ወንጀሎች ነበሩ፡፡ በሰለጠነው ዓለም የሕዝብን ድምፅ ከመስረቅ በላይ ወንጀል የለም፡፡ እዚህ ላይ ሁለት ነገሮችን አስታውሼ ልለፈው፡፡ በኢህአዴግ -1- ዘመን አቶ በረከት፤ ኢህአዴግ ከስድስት ሚሊዮን በላይ አባላት አሉትና በዝረራ ያሸንፋል ብሎ ሲያስቸግረኝ፤ አቶ በረከት፤ ኢህአዴግ ሁለት ምኩዞች አሉት፤ አንደኛው ምርጫ ቦርድ ነው፡፡ ሁለተኛው ጠመንጃችሁ ነው፡፡ ሁለቱን ምርኩዞቻችሁን አስቀምጣችሁ ተቃዋሚዎችን ካሸነፋችሁ፤ እኔ በግሌ እናንተ የሚትሉትን 20 ና 30 ዓመታት ብቻ ሳይሆን፤ ለሃምሳ ዓመታት እንዲትገዙን እፈርምልሀለሁ እንዳልኩት አሰታዉሰለሁ፡፡ በኢህአዴግ -2- ጊዜ ደግሞ ዶ/ር አቢይ በጠሩት ድንገተኛ ስብሰባ ላይ ገለልተኛ የሆነው ጠቋሚ ኮሚቴ ስምንት ሰዎች አጣርቶ ስላቀረበ አራት ሰዎች መመረጥ ስላለባቸው በተጠቆሙት ሰዎች ላይ አስተያየት ስጡ አሉን፡፡o ሌሎች ስብሰባው ላይ የተገኙ የየድርጅት መሪዎች ያሉትን ብሎዋል፤ እኔ ጨዋታው ስላላማረኝ፤ አብዛኛዎቹን ዕጩዎች ብዙዎቻችን አናዉቃቸውምና ከየት እንደመጡ እንኳ ለማወቅ የ24 ሰዓት ጊዜ ስጡኝ ብዬ አጥብቄ ጠየኩኝ፡፡ ዶ/ር አቢይ አይቻልም አሉ፡፡ ነገ የምናገረው እንዳይጠፋኝና ለታሪክም ቢሆን ተአቅቦ (reservation) መዝግቡልኝ ማለቴ ትዝ ይለኛል፡፡ ምስክሮችም አሉኝ፡፡o የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ መጥቶ የምርጫ ቦርድ ኃላፊዎች፤ የምርጫ ጊዜውን ሰሌዳ ለማስተላለፍ በጠሩት የምክክር ስብሰባ ላይ እንደተናገርኩኝ፤ መለኮታዊ ጣልቃ ገብነት (devine intervention) ነው እንዳልኩኝ ምርጫው ባይተላለፍ ኖሮ የአዲሱ ምርጫ ቦርድ አካሄድ ሌላ ከበድ ቀውስ ሊያስከትል ይችል እንደነበረ ዛሬ ላይ ሆኜ በእርግጠኝነት መናገር እችላለሁ፡፡ ይህንኑ ዳግም ብዙ ጊዜ በታጋይነቷ ለምናውቃት ክብርት ብርቱኳንም ጭምር መናገሬን አስታውሳለሁ፡፡ስለሆነም የሚመጣውን ምርጫ አዲስቷን ዴሞክራትክ ኢትዮጵያ እንድትወለድበት ካላደረግን፤ የንጉስ የማክያቬሊ ምክር፣ የመንግስቱ ኃይለማርያም፣ የጆሴፍ ስታሊን ቀይ በትር፣ የመለስ ዜናዊ፣ የሊቀ መንበር ማኦ አብዮታዊ ዴሞክራሲ ውሰት፤ ኢትዮጵያን ለመለወጥ የታሪክ ፈተናውን ለማለፍ እንዳለስቻለቸዉ፤ የዶ/ር አቢይም የመደመር የፖለቲካ ቀመር አዛውንቱ የፈረንጅ ምሑር የሚለውን የኢትዮጵያ ፖለቲካ የመጨረሻ ሁለት ድንበሮችን የሚያሻግረን አይመስለኝም፡፡ እሱን ካልተሻገርን ደግሞ ሁሌም እንደምለው ለሁላችንም የሚትሆን ዴሞክራትክ ኢትዮጵያ የምትፈጠር አይመሰልኝም፡፡ከማጠቃለሌ በፊት፤የብሔረታዊ መግባባቱ የፖለቲካ ጥራታችን ይሳካ ዘንድ መፍትኼ የሚሹ ቁልፍ ጉዳዮች ላስቀምጥ፡
1. ያለ ሀገራዊ ስምምነት በዋናነት በአንድ ቡድን ሕልምና ፍላጎት (በተለይ የአንድ ቡድን ፍኖተ ካርታ (road map) የመመረቱ ጉዳይ ለዉጡን አጣብቂኝ ዉስጥ ማስገበቱን የማወቅ ጉዳይ፤2. ለውጡን ለማምጣት በዋናነት የላቀ አስተዋጽኦ ያላቸው ኃይሎች (ለምሳሌ እንደ ኦሮሞ ቄሮ ዓይነቶቹ) ወደ ዳር የመገፋታቸው ጉደይ፣
3. ለውጡን እየመራ ያለው ከራሱ ከኢህአዴግ የወጣ ቡድን ቢሆንም፤ በለውጡ ምንነት፤ ፍጥነት፣ ስፋትና ጥልቀት ላይ የተለያዩ የኢህአዴግ ክንፎች ስምምነት ማጣታቸውና በዚህም ምክንያት እያመጣ ያለው አደገኛ ሁኔታ፣
4. በሚጋጩ ሕልሞቻችን ምክንያት ላለፉት 50 ዓመታት መፍትኼ ያለገኘንለት የመከፋፈል ፖለቲካችን (political polarization) ጉዳይ፤
5. ዴሞክራሲያዊ ለውጡ ለአብዘኛዉ የኢትዮጵያ ሕዝቦችና የፓለቲካ ሃይሎች ተቀበይነት ያለዉ፤ ሠላማዊና የተሳካ እንዲሆን የጋራ ፍኖተ ካርታ (road map) የመቀየስ አስፈለጊነት ጉደይና፤ የተቀየሰዉን በጋራ ሥራ ላይ የማወል ጉደይ፤
6. ነፃና ፍህታዊ ምርጫ ማለት በእርግጥም በሕዝቦች ይሁንታ ላይ የተመሰረተ የፓለቲካ ጨወታ መሆኑን የመረደት ጉዳይ፤
7. ሀገራችን እዉነተኛ ዲሞክራሲያዊ የፈድራል ሥርዐት ያስልጋታል ስንል፤ ከሕልሞቻችን በሻገር በሕዝቦቻችን ፍላጎት ለይ የተመሰረተ የፖሊቲካ ሥርዓት መሆኑን የማረጋገጥ ጉዳይ፡
8. ብሔራዊ መግባባቱ በተሻለ መንገድ የሚሳካው፤ በደቡብ አፍሪካ እና ኮሎምቢያ በመሰሰሉት
9. ሀገሮች እንዳየነው የፖለቲካ እስረኞችንና የጫካ አማፅያንን መጨመርን የማስፈለጉ ጉዳይ፤
10. የተሰካ ብሔራዊ እርቅን ለመምጠት ከሥልጠን በሻገር የምር የፖለቲካ ቁረጠኝነት (political will)
11. የማስፈለጉ ጉዳይ፤
12. ስለኢትዮጵያ አንድነት ያለን ግንዘቤ ከፊታዉራሪ ሀብተጊዮጊስ እይታ የሳፋና ለሀገርትዋ ያለን ፍቅርም ገደብ የማድረጉ ጉደይ ናቸዉ፡፡በመደምደሚያዬም እዚህ ያደረሰንን ያገራችንን ፖለቲካ ጉዞ ታሪክ ወደኋላ እያየሁ፤ የወደፊቱን የሀገራችንን ዕጣ ፋንታንም እያማተርኩ ለጠቅላይ ሚኒስትሩም፣ ለሁላችንም የታሪክ የግርጌ ማስታወሻ ልተዉ፡፡ በቅርብ ቀን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ አትፈርስም፤ ኢትዮጵያን የሚያፈርሷት እኛን ቀድሞ ሲያፈርሱ ነው፤ ኢትዮጵያን ለማፍረስ አይፈቀድላቸውም ሲሉ አዳምጫለሁ፡፡ ሀገርን ለመፍረስ የሚፈልጉ ሃይሎች መጀመሪያኑ ፈቃድ ይጠይቃሉ፤ አይጠይቁም የሚለዉን ክርክር ውስጥ ሳልገባ፤ በጨዋ ቋንቋ ንግግራቸውን አልወደድኩላቸውም፡፡ ንግግራቸውንም ተከትሎ የኢሳት ቴሌቪዥን የፖለቲካ ተንታኞች የሚታወቁ የአዛውንት ምሁርን በመጥቀስ (ይህኑን ምሁር መንግስቱ ሀይለማርያምም ያዉቃል ብለን ስለተሰሩ የንጉሱ በለስልጠኖች ምክር ጠይቀነዉ፤ ጠመንጃዉ በእናንተ እጅ ነዉ፤ የምን ምክር ትጠይቁናላችሁ ብሎኛል ማላቱን አንብበለሁ) ዶ/ር አቢይ ጥሩ ይዘዋል፤ ሕጉንም ሰይፉንም እየተጠቀሙ ነው ያሉት የበለጠ ሥጋት ፈጥሮብኛል፡፡ እዚህ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጨምሮ ሁላችንም ደጋግመን ማሰብ ያለብን ጨዋታው ከተበላሸ አብዛኛው ዓለምን በሰዓታት ውስጥ ወደ አመድነት የሚለወጥ ወይም ሕይወት አልባ ሊያደርግ የሚችል የኑክለየር መሳርያ የታጠቀ፤ ነፍሷን ይማርና የሶቭዬት ህብረት ሠራዊት ዓይኑ እያየ አገራቸው መበቷን ነው፡፡የሀገራችንን ፖለቲካ በጋራ አስተካክለን ሁላችንንም በእኩልነት የምስታስተናግድ ዴሞክራቲክ ኢትዮጵያን ለመፍጠር እግዚአብሔር ይርዳን እላለሁ፡
ዋቢ መፃሕፍት:
1. Bahiru Zewde (1991) A History of Modern Ethiopia, 1885 -1991.
2. Gebru Tareke (1996) Ethiopia: Power and Protest, Peasant Revolts in the Twentieth Century.
3. John Markakis, (2011) Ethiopia: The Last Two Fronties.4. Merera Gudina, (2002) Ethiopia: Competing Ethnic Nationalisms and the Quest for Democracy, 1960-2000.5. Teshale Tibebu, (1995), The Making of Modern Ethio896-1974.
Ethiopia: Talk of the town: The Meaningless Change of Abiy Ahmed Ali August 23, 2020
Posted by OromianEconomist in Uncategorized.add a comment
Talk of the town: The Meaningless Change of Dr. Abiy
By Faisal Roble
As far back as June 2018, I gave an interview to the BBC Somali Section and critically appraised Abiy and his change. While most people and commentators were enamored by Dr. Abiy’s oratory, sermon-like speeches, and pan-Ethiopian patriotism, I saw then a dark side of Dr. Abiy.
How did you see that, you may ask? Just a quick context: throughout the 1990s, while writing essays and columns for the now defunct Ethiopian Review based then at Los Angeles, l used to spend quarrelling time with a lot of Ethiopians. We used to have heated debates. Most of the time, I will be the only Somali and lowlander. It was then that I picked and learned code words for greater Ethiopia and the politics of pan-Ethiopian nationalism, or even chauvinism.
Words like the soul of Ethiopia (ya Itiyobiya li olawinet), the absolute unity of Ethiopia (ya Itiyobiya andenet fisuminat) are some of the code phrases you could hear uttered by the likes of the late Dr. Asarat (former leader of the All Amhara Party), Goshu Wolde (Leader of Madhin Party), and one Dr. Taye who in the 1980s headed Ethiopia’s teacher’s trade union.
The first time I heard Dr. Abiy speak, I was able to easily pick these highly charged phrases from his otherwise well-orchestrated speeches in Amharic. Also, my long-time residence in the US sensitised me to all the cleverly ways evangelists and priests use religious sermons for sending political messages, especially by right wing evangelists. I saw both attributes in Dr. Abiy’s speeches. He was invoking nationalist sentiments by often delivering them in a sermon style. This combination mesmerised and disarmed people in need for a heavenly deliverance.More than any group, Somalis fell for him.
Somalis both inside the Ethiopian empire as well as those in the Federal Somali Republic gave in to the charms of Dr. Abiy. Often people like me were small minorities. Today, the reality on the ground is different. I feel exonerated but not happy for all the hardship we have to again face.
The world is almost about to abandon Dr. Abiy. Traces of facts are emerging from key EU members who are thinking of cutting him lose. Germany, Sweden, Denmark, Belgium, and several other EU countries are already letting managed leaks go out regarding their disappointment with their earlier infatuation with Dr. Abiy. Also, some key US congressional members are speaking out publicly (see attachment bellow).
Not only did he lose the Oromo, but he is killing, torturing, and evicting them from their lands. Almost 2/3 of the OLF leadership is in jail. Other key Oromo leaders such as Jawar Mohamed, Dr. Bakale Garba, and many more are in jail. The most vocal Amhara critic (Lidatu) is not only in jail but tortured severely.
According to one account, schools, community centres and even centres that used to deliver social services in Oromia region are converted into jails.
The level of mayhem taking place in Oromo region within a short period of time is unprecedented in Ethiopia.Is this something that should worry other groups, particularly Somalis? Where does the current reality place the pact between ONLF and OLF? These are not normal times in Ethiopia and as such, no one should put their eggs in one basket. The Somali region is still singing praise songs for the Prime Minister and his phantom “Prosperity Party.” They need to stop that. What prosperity can one talk about when the soil of the countryside that used to give seeds and sustenance to the multitude is burning?
There is a need for the Somalis to do several small but decisive things that would help them sail through this tough time:
(1) Do not let Somali Liyo police be used in the current ongoing mayhem against Oromo.
(2) Distance yourself from Arat Killo (Palace) as much as possible and reclaim your federal status. You are primarily responsible for the welfare of your constituency.
(3) Strengthen internal cohesion and institutionalize your collaboration with all groups in the region while showing sympathy to those in the fire. Don’t make the theory of “history repeats itself” play out here where lack of unity pits one against another.
You must be logged in to post a comment.