jump to navigation

Ethiopia: Following the Prime Minister’s statement, looting by his security forces intensified in Oromia September 18, 2020

Posted by OromianEconomist in Uncategorized.
trackback

“Police are allowed to seize money from a person who has deposited more than one million birr in his house,” the prime minister said in a statement three days ago. Following this statement, looting intensified throughout Oromia. The regular police and special police forces are stopping public transport vehicles on the road, searching the passengers and looting their money. There is no difference in the amount of money the police is looting. A person with three thousand birr is robbed. Five thousand birr will be looted. Ten thousand birr will be looted. Twenty thousand birr will be looted. Fifty thousand birr will be looted. We are even hearing that someone has been robbed of a thousand birr. 1000 Birr = 27 US Dollar

The robbery does not take place in one place. Security forces in all Oromia zones and districts are looting the public in broad daylight. The government security forces are robbing people who drive public transport with a small amount of money for personal use.

Following the Prime Minister’s statement, looting intensified throughout Oromia. አስደንጋጭ ዝርፊያ በኦሮሚያ

አስደንጋጭ ዝርፊያ በኦሮሚያ

—አፈንዲ ሙተቂ– Afendi Muteki

የሚካሄደው ነገር ሁሉ “የህግ ያለህ! የሀገር ያለህ! የመንግሥት ያለህ!” የሚያሰኝ ነው። “2013 እንደ 2012 እንደማይሆን ተስፋ እናደርጋለን” ብንልም ገና ከጅምሮ ተስፋ የሚያጨልም ዘረፋ ተፈጥሮብናል። ድሮ ዘረፋ የሚያካሄደው ሆን ብሎ በዚህ ተግባር ላይ የሚሰማራ የጥፋት ሃይል ነበር። አሁን ግን መንግሥት ራሱ ጸጥታን እንዲያስከብር ያሰማራው ሃይል የዘረፋ ፊት አውራሪ ሆኖ ተከስቷል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሶስት ቀን በፊት የብር ኖቶች እንደሚለወጡ ባስታወቁበት መግለጫቸው “ፖሊሶች ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ በቤቱ አስቀምጦ የተገኘን ሰው ገንዘብ እንዲወርሱት ተፈቅዶላቸዋል” ብለው ነበር። ታዲያ ይህንን ቃል ተከትሎ በመላው ኦሮሚያ ዝርፊያ ተጧጡፏል። መደበኛው ፖሊስ እና ልዩ ፖሊስ የሚባለው ሃይል በመንገድ ላይ የሚጓዙ የህዝብ ማመላለሻ መኪናዎችን እያስቆሙ ተሳፋሪውን ፈትሸው ያገኙትን ገንዘብ እየዘረፉ ይገኛሉ።ፖሊሶቹ የዘረፋ ዒላማ በሚያደርጉት ገንዘብ ላይ የመጠን ልዩነት የለም። ሶስት ሺህ ብር የያዘ ሰው ይዘረፋል። አምስት ሺህ ብር የያዘም ይዘረፋል። አስር ሺህ ብር የያዘም ይዘረፋል። ሃያ ሺህ ብር የያዘም ይዘረፋል። ሃምሳ ሺህ ብር የያዘም ይዘረፋል። ሌላው ቀርቶ አንድ ሺህ ብር የተዘረፈ ሰው መኖሩንም እየሰማን ነው። የሚካሄደውን ዝርፊያ ያየ ሰው “ገንዘብ በእጅ መያዝ ተከልክሏል” የሚል አዋጅ የወጣ ነው የሚመስለው።ዝርፊያው በአንድ ቦታ ብቻ የሚካሄድ አይደለም። በመላው የኦሮሚያ ዞኖችና ወረዳዎች የጸጥታ ሃይሎች በጠራራ ጸሐይ የማኅበረሰቡን ገንዘብ እየቀሙት ነው። እርግጥ በህገ ወጥ መንገድ የሚንቀሳቀስ ገንዘብ መቆጣጠር በየትኛውም ሀገር የሚታወቅ አሰራር ነው። በተለይም ብዙ መጠን ያለው ገንዘብ ከቦታ ቦታ ሲዘዋወር ከሚያደርሰው የዋጋ ግሽበትና የኢኮኖሚ መደንበሽ አንጻር ቁጥጥር ሊደረግበት ይገባል። የውጪ ምንዛሬ ላይም ተመሳሳይ ቁጥጥር ይደረጋል።አሁን በኦሮሚያ የሚካሄደው ግን ከዚህ ፈጽሞ የተለየ ነው። ለግል መገልገያ የሚጠቅማቸውን መጠነኛ ገንዘብ ይዘው በህዝብ በመኪና የሚጓዙ ሰዎች ናቸው የዘረፋው ዒላማ እየሆኑ ያሉት። ሰሞኑን የወጣውን የብር ቅያሬ አዋጅ ተከትሎ ውስጥ ውስጡን “የወያኔዎችን የገንዘብ አቅም ለማዳከም የወጣ ውሳኔ ነው” የሚል ወሬ ሲሰማ ነበር። በእነዚህ ሁለት ቀናት ውስጥ የሚካሄደው ዝርፊያ ሲታይ ግን ብር የመቀየር ውሳኔውም ሆነ አፈጻጸሙ የኦሮሞን ሀብት ዘርፎ ህዝቡን ወደ ድህነት ለማስገባት ሲባል የወጡ ነው የሚመስሉት።—ገዥዎቻችን ህዝቡን ለመቆጣጠር ያስችለናል ያሉትን እርምጃ ሁሉ እንደሚወስዱ እናውቃለን። ሆኖም አንዳንዱ እርምጃ backfire አድርጎ ሀገሪቱን ወደ anarchy ሊያስገባ እንደሚችል የሚገነዘቡ አልሆኑም። አሁን በኦሮሚያ የምናየው የገንዘብ ዝርፊያ anarchy እንዲፈጠር አይነተኛ መንስኤ ሊሆን ይችላል። anarchy ከመጣ ደግሞ ከማንም ቀድመው የሚጠፉት ገዥዎቹ ራሳቸው ናቸው። ሀገሪቱም ትፈራርሳለች። ስለዚህ መንግሥት ነኝ የሚለው ሃይል ለራሱ ህልውና ሲል ይህንን ዝርፊያ በአስቸኳይ ሊያስቆመው ይገባል።

—-ግልባጭ — ለሀገር ውስጥና ለውጪ ሚዲያዎች

— ለኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን– ለኢትዮጵያ እምባ ጠባቂ ተቋም.

Comments»

No comments yet — be the first.

Leave a comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.