Finfinne on the 2nd of #HacaaluuHundeessaa’s assassination: Government sponsored mass attacks on Oromo. #OromoProtests July 16, 2020
Posted by OromianEconomist in Uncategorized.Tags: Genocide against the Oromo, Hacaaluu Hundeessaa
trackback
#ሃጫሉ ተሰውቶ በሁለተኛው ቀን ፊንፊኔ ውስጥ የታየውን እጅግ አደገኛ ነገር የሚያወራልህ የለም። ምክንያቱም የኦሮሞ ህዝብ ላይ የሚፈፀም ነገር ሁላ ኢትዮጵያ ውስጥ ትክክል ተደርጎ ይወሰዳል። ፊንፊኔ ውስጥ ምን ነበር የታየው?
1) በተደራጆ ዘረኞች የኦሮሞ ተወላጆች መኖሪያ ቤቶች እና ተቋማት ላይ ያነጣጠረ ዘረፋ እና የንብረት ውድመት ተከስቷል። በ መገናኛ 24 አካባቢ የኦሮሞ ተወላጆች ላይ አካላዊ ጥቃት ተፈፅሟል። የሪፍት ቫሊ ዩኒቨርስቲ ህንፃዎች ተሰባብሮ ንብረት ተዘርፏል። የኦሮሚያ ስም ያላቸው ባንኮች ላይ አንዳንድ ቦታዎች ላይ ጥቃት ተፈፅሟል።
2) ከሁሉም በላይ ያስደነገጠኝ ኦሮሞ ላይ ያነጣጠረ የመንግሥታዊ ሽብር ነበር። ነገሩ እንዲህ ነው – በመንግሥት አካካላት በኩል አንዳንድ ሰዎች ከየአካባቢው ተመርጠው የአካባቢያቸውን ነዋሪ እንዲያደራጁ እና ከኦሮሞ ራሳቸውን እንዲከላከሉ ይነገራቸዋል። በአካባቢያችንም ይህ የተነገራቸው ሰዎች ስብሰባ ጠሩን። እኔ ለስብሰባ ስንጠራ የመሰለኝ ቤት እየለዩ ስለሚያጠቁት እና ስለሚዘርፉ የተደራጁ ሰዎች ለመነጋገር መስሎኝ ነበር ነገሩ ሌላ ነው። ቃል በቃል ያሉት ነገር ቄሮ እና በከተማው ዙሪያ ያሉት ገበሬዎች ወደ ከተማው እየመጡ ስለሆነ በምንችለው ሁሉ መከላከል አለብን። ፊሽካ ጡሩምባ እና አላርም ይዘጋጅ። መምጣታቸው ከታወቀ ድምፅ በማሰማት እን ስብስብ እና እንመክት አሉ። አንዳንዶቻችን ይህ ነገር የእርስ በርስ ጦርነትን የሚቀሰቅስ አደገኛ ሁኔታ መሆኑን ለመናገር ሞከርን። ባደረግነው ውይይት መጨረሻ ላይ ንብረታችንን እና ቤተሰቦቻችንን ከማንኛውም የተደራጀ ኃይል እንጠብቅ በሚለው ተስማምተን ነበር። ሆኖም ግን ተወያይተን ወደ ቤት ከገባን እየመጡ ነው… እየመጡ ነው…እየመጡ ነው ከሚል ጩሃት ጋርበ ፊሽካ ተነፍቶ ጊቢያቸውን መጠበቅ ሳይሆን ተሰባስበው ወደ ዋናው መንገድ ሄዱ። ደግነቱ ፍርሃት እና ጥላቻ የወለደው የራሳቸው ጥላ እያስፈራራቸው እንጂ የመጣ ነገር አልነበረም።
ይህ እንግዲህ #ፊንፊኔን ከኦሮሞ የመጠበቅ ፕሮጀክት አንዱ ክፍል ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ሚዲያዎች በሙሉ እና የመንግሥት አካላት የኦሮሞ ህዝብን #ለጄኖሳይድ የማዘጋጀት ሂደቱን በተቀናጀ ሁኔታ እየሠሩበት ነው።
Comments»
No comments yet — be the first.